ግብርና ሚኒስቴር ዘርፉን ለማዘመን ከሦስት ተቋማት ጋር ስምምነት ተፈራረመ

0
1569

ግብርና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ እና ኢትዮሊዝ ከተሰኘ የካፒታል ዕቃዎች አቅራቢ ድርጅት ጋር ግብርናን ለማዘመን/ሜካናይዝድ ለማድረግ በታቀደ የመግባቢያ ሰነድ ላይ ስምምነት አደረገ።

ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት አጠቃላይ የግብርና አሰራር በመውጣት ሰፋፊ መሬቶች ላይ ቴክኖሎጂን በመጠቀም፣ በድኅረ ምርት አሰባሰብ የሚያጋጥሙ የምርት ብክነትን በመቀነስ የግብርናውን ክፍለ ኢኮኖሚ ለመቀየር እየሠራች ሲሆን፣ ስምምነቱ ጥልቅ የገንዘብ አቅም የሚጠይቁ የግብርና መሣሪያዎችን ለማቅረብ የሚያስችል ነው።

ኢትዮ ሊዝ ባሳለፍነው ኅዳር ወር ሥራውን በይፋ የጀመረ ሲሆን፣ እስከ አሁን ድረስ በፓይለት ፕሮጀክቶች ላይ ስምንት ግዙፍ ጄነሬተሮች እና ዘጠኝ ትራክተር ለግብርናው ዘርፍ አቅርቧል። በቀጣይም 48 ትራክተሮችን ወደ አገር ውስጥ በማስገባት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።

በቀጣይም ኢትዮ-ሊዝ በያዘው 400 ሚሊዮን ብር በጀት በአገራችን የሜካናይዜሽንን ሥራ አጠናክሮ እንደሚሠራ እና አርሶ አደሮችም የእርሻ መሣሪያዎችና የተለያዩ ግብአቶች እንደሚያቀርብ የተገለፀ ሲሆን፣ መንግሥት አሠራሮች ቀልጣፋ ማድረግ እንደሚገባው ድርጅቱ አሳስቧል።

የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ የግብርናውን ክፍለ ኢኮኖሚ ለማሳደግ እየሠራ የሚገኘው የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ በበኩሉ፣ በግብርናው በኩል ያሉትን ችግሮች በመለየት 300 ወረዳዎች የኩታ ገጠም እርሻ እንዲጠቀሙ ማድረጉን ገልጿል።

ኤጀንሲው 10 የሚደርሱ እያንዳንዳቸው 9 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ ሙሉ የሜካናይዜሽን ሰርቪስ ሊሰጡ የሚችሉ ተቋማት መገንባቱን በመግለፅ፣ በቀጣይም በርካታ ሥራዎችን ከግብርና ሚኒስቴር እና ከኢትዮ-ሊዝ ጋር በጋራ እንደሚሠራ አስታውቋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 69 የካቲት 21 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here