ብርሃንና ሰላም ሊያደርግ ያሰበውን የዋጋ ጭማሪ ሰረዘ

0
666

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት በጋዜጦች ኅትመት ዋጋ ላይ ሊጨምር አስቦ የነበረውን መሰረዙ ታወቀ።
የድርጅቱ ማኔጅመት ከቦርዱ ዕውቅና ውጪ ሊያደርግ ያሰበው ጭማሪ በድርጅቱ ሠራተኞች የውስጥ ሐሳብ ክፍፍል ምክንያት ሊሰርዝ መቻሉ ታውቋል። “የተሟላ አገልግሎት መስጠት ባልቻልንበት ሁኔታ እንዴት ዋጋ እንጨምራለን” በሚል የአቋም ልዩነት ባንፀባረቁ ጥቂት ሠራተኞች ምክንያት ሥምምነት ላይ ባለመደረሱ የታሰበው ጭማሪ እንዲሰረዝ ተደርጓል።
ድርጅቱ ኅዳር 25 ለአሳታሚ ድርጅቶች በበተነው የስብሰባ ጥሪ ደብዳቤ ላይ እንደተጠቀሰው በዓለም ላይ የፐልፕ ዋጋ መጨመሩ ታሳቢ ያደረገ መሆኑ ታውቋል። ይሁንና በታሰበው ቀን ስብሰባው አልተካሔደም።

ቅጽ 1 ቁጥር 4 ኅዳር 29 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here