የታሸገ ውሃ እና ለስላሳ መጠጦች ቅናሽ ሊደረግባቸው ነው

0
1438

አዲሱን የኤክሳይስ ታክስ አዋጅ መፀድቅን ተከትሎ የታሸገ ውሃ እና ለስላሳ መጠጦች ላይ የተፈጠረውን የዋጋ ጭማሪ ለማስተካከል፣ አምራቾች እና አከፋፋዮች ከገቢዎች ሚኒስቴር እና ከንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጋር በመነጋገር የዋጋ ቅናሽ ሊያደርጉ ነው።

የለስላሳ መጠጦች ላይ በማምረቻ ዋጋ ሲሰላ የነበረው ኤክሳይስ ታክስ ወደ ፋብሪካ መሸጫ ዋጋ በመቀየሩ ምክንያት፣ የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ አንዳንንድ ቸርቻሪዎች ከዐስር እስከ ዐስራ ኹለት ብር ይሸጥ የነበረውን፣ እስከ አስራ ዘጠኝ ብር ከፍ ማድረጋቸው ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ነው። በመሆኑም የዋጋ ማስተካከያ ማድረግ አለባቸው ሲል የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል።

ንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በበኩሉ፣ የተደረገውን የዋጋ ጭማሪ በማስመልከት ባደረገው ጥናት፣ ቀደም ሲል ከስድስት እስከ ሰባት ብር ሲሸጥ በነበረው የታሸገ ውሃ ላይ ከኹለት እስከ ሦስት ብር ጭማሪ ታይቷል። ከስልሳ እስከ ስልሳ ኹለት ብር የማከፋፈያ ዋጋ የነበረው የታሸገ ውሀም፣ ሃምሳ አራት ብር የማከፋፈያ ዋጋ ወጥቶለት እንዲሸጥ ተደርጓል።

ቅጽ 2 ቁጥር 70 የካቲት 28 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here