የስፖርት ዉርርድ ማኅበር ማኅበራዊ ኃላፊነቴን እየተወጣሁ ነው አለ

0
529

የስፖርት ውርርድ ማኅበር የካቲት 26/2012 ለጋዜጠኞች በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ወጣቶችን ካልተፈለገ ሱስ ወጥተዉ የመዝናኛ ጊዜያቸዉን በስፖርት የውድድር ቤቶች እንዲያሳልፉ በማድረግ ማኅበሩ አገራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሆነ አስታውቋል።

ስፖርት ዉርርድ ማኅበር በሰጠዉ መግለጫ፣ በማኅበራዊ ሚዲያ ስለ ዘረኝነትና ጥላቻ የሚጽፉትን ስፖርት ቤቲንግ መቀነስ መቻሉን አመላክተዋልል። በመግለጫዉ ላይ ከጋዜጠኞች ጋር ውይይት የተካሄደ ሲሆን፣ ማኅበር በርካታ ሐሳቦችን አንስቷል። ከዚህም በተጨማሪ 14 ከሚሆኑ ከስፖርት ቤቲንጎች ባለቤቶች ጋር የጋራ ማኅበር መመሥረታቸውም ተገልጿል።

“ስፖርት ቤቲንግ ቁማር አይደለም። ለአገራችን ከፍተኛ ጥቅም አለው። በአሁን ሰዓት ብቻ 1800 ለሚደርሱ ሥራ አጥ ወጣቶች የሥራ እድል ፈጥረናል። ለበርካታ በጎ አድራጎት ድርጅቶችም ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።›› ሲል ማኅበሩ ገልጿል።

‹‹ከ18 ዓመት በታች ያሉት እንዲጫወቱ አይፈቀድም። ለዚህ ደግሞ መታወቂያ እያየን ነው የምናስገባው።” በማለትም የማኅበሩ ሊቀመንበር ሚካኤል ደምሰው ተናግረዋል። አክለውም አጓጉል ሱስ ውስጥ ገብተው የነበሩ ልጆችን ከሱስ እንዲላቀቁ አድርገናል ያሉ ሲሆን፣ ወጣቶች የስፖርት ፍቅር እንዲኖራቸው እና በስፖርታዊ ጉዳዮች ላይ እንዲወያዩ በማድረግ ከአልባሌ ነገሮች እንዲርቁ ቤቲንግ ምክንያት መሆኑንም ገልፀዋል።

የሴቶች ሕፃናት እና ወጣቶች ሚኒስቴር በአገራችን የሚገኙ ማኅበራዊና ባህላዊ ትስስሮች እንዲላሉና እንዲሸረሸሩ፣ የእምነት ስርአቶች እንዳይከበሩ፣ አገር በቀል እውቀቶች እንዲዳከሙ አድርጓል በሚል ድርጊቱን እየተቃወመው ይገኛል።

ጠቃሚ ባህሎችን እና ልማዶችን ለትውልድ ማስተላለፊያ ስርአቶች እንዲሁም ማኅበረሰባዊ የመደጋገፍና የመረዳዳት ልምዶች በግለኝነት አስተሳሰብ ምክንያት ለከፍተኛ አደጋ እንዲጋለጡ እያደረጋቸው መሆኑንም በሚኒስትሩ ሲገለፅ ቆይቷል።

ቅጽ 2 ቁጥር 70 የካቲት 28 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here