ማልታ ጊነስ ለኢትዮጵያ ልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ የኹለት ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገባ

0
918

ድርጅቱ ከማልታ ጊነስ የፕላስቲክ እና የጠርሙስ ምርቶች ሽያጭ ላይ ተቀንሶ የሚሰበሰበው ኹለት ሚሊዮን ብር ለኢትዮጵያ ለልብ ህሙማን ሕፃናት መርጃ በድጋፍ መልክ እንደሚለግስ አስታውቋል።

ገንዘብ የማሰባሰብ ተግባሩ ‹‹መልካምነትን እንጋራ›› በሚል ርዕስ፣ በክርስትና እና እስልምና እምነቶች የፆም ወቅት የሚካሄድ እና ደንበኞቹን በበጎ ተግባር ላይ የሚያሳትፍ የመልካምነት እንቅስቃሴ ጀምሯል።

የ‹‹መልካምነትን እንጋራ›› እንቅስቃሴ ዋነኛ ዓላማ፣ ለበጎ ተግባር የሚለገስ ኹለት ሚሊዮን ብር መሰብሰብ ሲሆን፣ በሦስቱ ተከታታይ የፆም ወራት፣ ከማልታ ጊነስ የፕላስቲክ እና የጠርሙስ ምርቶች ሽያጭ ላይ ተቀንሶ ለኢትዮጵያ ለልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ በድጋፍ እንደሚደረግ ድርጅቱ አስታውቋል።

በአሁኑ ወቅት 7 ሺሕ የሕክምና ተራ ጠባቂዎች ያሉት የኢትዮጵያ የሕፃናት የልብ መርጃ፣ በአቅም ውስንነት ምክንያት በየዓመቱ 500 የልብ ታካሚዎችን ብቻ እያስተናገደ ይገኛል። ተመዝግበው ተራ በመጠባበቅ ላይ የሚገኙትን ሰባት ሺሕ ሕጻናት ለማስተናገድ 14 ዓመታት ይፈጃል።

ከኹለት ሚሊዮን ብር ድጋፉ በተጨማሪ ማልታ ጊነስ በድርጅቶች መካከል የማልታ ወዝወዝ ዳንስ ውድድር በማዘጋጀት፣ የወዝወዝ በማልታን ዳንስ የደነሱበትን ተንቀሳቃሽ ምስል የማልታ ጊነስን የፌስቡክ ገፅ ሥም “ታግ” አድርገው ለሚለጥፉ 10 ድርጅቶች፣ በእያንዳንዳቸው ሥም ለኢትዮጵያ የሕፃናት የልብ መርጃ ማእከል 20 ሺሕ ብር እንደሚለግስ ቃል ገብቷል።

ቅጽ 2 ቁጥር 71 መጋቢት 5 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here