የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር በለይቶ ማቆያ እንደሚገኙ ተገለፀ

0
632

ተቀማጭነቱን በአዲስ አበባ ያደረገው አፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ዋና ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪመሃማት የቅርብ የስራ ባልደረባቸው በኮሮና ኮቪድ 19 መያዙን ተከትሎ በለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲገቡ መደረጉ ይፋ ሆኗል። ከዚሁ ጋር ተያይዞም ኮሚሽኑ ሙሳፋኪን ጨም ሌሎች ኹለለት የስራ ባልደረቦቻቸውንም በለይቶ ማቆያ ውስጥ ማስገባቱን አስታውቋል።

ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው÷ የኮሚሽኑ የጤና ዘርፍ ዳይሬክቶሬት የኮሮና ኮቪድ 19 ወረርሽኝ ከተሰማበት ጀምሮ ጉዳዩን ሲከታተል መቆየቱን እና አሁንም እየተከታተለ እንደሚገኝ አስታውቋል።አያይዞም በኮሚሽኑ ውስጥ ሰራተኛ በሆነ አንድ ግለሰብ ላይ ቫይረሱ መገኘቱንና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያሉት ሰዎችም በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ገልጿል። ቫይረሱ የተገኘበት የኮሚሽኑ ሰራተኛ በኢፌዲሪ የጤና ሚንስቴር አማካኝነት ተገቢውን ክትትል እየተደረገለት ሲሆን ከታማሚው ጋር ቀጥተኛ ንክኪ የነበራቸው የኪሚሽ ሰራተኞች እና ግለሰቦች በአፋጣኝ በዳይሬክቶሬቱ በኩል ይፋ በሆኑ አድራሻዎች ማሳወቅ እንደሚኖርባቸው ኮሚሽኑ አሳስቧል።

ቅጽ 2 ቁጥር 73 መጋቢት 19 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here