10ቱ በርካታ የሕክምና ባለሞያዎች የሚገኙባቸው አገራት

0
478

የዓለማችን ተመራጭ የጤና አጠባበቅ ስርዓት በርካታ የሕክምና ባለሞያዎች ባሉበት የሚገኝ ነው ብለው የሚሟገቱ አሉ። መረጃዎች እንደሚያሳዩትምየዓለም ጤና ድርጅት አባል ከሆኑ አገራት መካከል፣ ከ44 በመቶ በታች የሚሆኑት ብቻ ናቸው ለእያንዳንዱ አንድ ሺሕ ሰው ከአንድ በታች የሕክምና ባለሞያ ወይም ዶክተር ያላቸው ሆነው ተመዝግበዋል።

ታድያ ከኹለት ዓመት በፊት በወጣው መረጃ መሠረት በዓለም ደረጃ ለአንድ ሺሕ ሰዎች 1.13 ዶክተሮ ብቻ ነው ያሉት። ወይም በተብራራ አነጋገር፣ አንድ ሺሕ ሰዎችን 1.13 የሚሆኑ የሕክምና ባለሞያዎች ናቸው የሚያክሙት እንደማለት ነው። ይህም በወቅቱ የዓለም ጤና ድርጅቱ ትንበያ ሲሰጥ፣ ዓለም 4.3 ሚሊዮን የጤና ባለሞያዎች እጥረት ያጋጥማታል ብለው ተንብየው ነበር።

ይህ ነገር አሁን ላይ መከሰቱ በጥናት የተረጋገጠ ባይሆንም፣ የኮሮና ቫይረስ በከባዱ እየፈተነ ያለው የሕክምና ባለሞያዎችን ሆኗል። ታድያ ወርልድ አትላስ ይህ የዛሬውን ወረርሽኝ መከሰት ሳይገምትና ሳያውቅ በፊት፣ በ2018 ባወጣው ዘገባ ኳታር ለዐስር ሺሕ ሰዎች ከሰባ ሰባት በላይ ዶክተሮች ያሏት አገር መሆኗን አስቀምጧል።

በመጠነኛ ልዩነት ደግሞ ሞናኮና ኩባ ይከተላሉ። ዝርዝሩ ካረፈበት ተጨማሪ ኻያ አገራት መካከል ግን አንድ እንኳ የአፍሪካ አገር አልጠቀሰም። ይህም ኻያኛ ላይ በ38.6 ዶክተሮች እስከተቀመጠችው አርጀንቲና ድረስ ነው።

ቅጽ 2 ቁጥር 75 ሚያዝያ 3 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here