የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ለመከላከል የሚውሉ ግብኣቶችን በአገር ውስጥ ምርት ሊሸፈኑ ነው

0
634

በኢትዮጵያ የተከሰተውን ኮቪድ 19 ወረርሽኝ ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የሚረዱ ቁሳቁሶችን በአገር ውስጥ ለማምረት እና ፍጆታውንም ለመሸፈን በሒደት ላይ መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መላኩ አለበል አስታወቁ።
በአሁኑ ወቅት 100 ሚሊዮን ሊትር ቴክኒካል አልኮል በየቀኑ እየተመረተ ነው ያሉት ሚኒስትሩ በሀገሪቱ ውስጥ የሚገኙ 43 የሳሙናና ዲተርጀንት አምራች ኢንዱስትሪዎች በተሻለ አቅም እንዲያመርቱ በማድረግ በሽታውን ለመከላከል የሚያስችሉ 2,258,200 ኪሎ ግራም ደረቅ ሳሙና እና 357,951 ሊትር ፈሳሽ ሳሙና በየቀኑ እየተመረተ ለገበያ እየቀረበ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
ሚኒስትሩ አክለውም የኢንዱስትሪዎቹን የጥሬ እቃ አቅርቦት ችግር በመፍታት በየቀኑ 3 ሚሊዮን ኪሎ ግራም ሳሙና እና 747,873 ሊትር ፈሳሽ ሳሙና ለማምረት የሚያስችል ስራ እየተሰራ መሆኑን የጠቆሙ ሲሆን የጥሬ እቃ አቅርቦት ችግሩን ሙሉ በሙሉ መፍታት ከተቻለ የሳሙናና ዲተርጀንት ፍላጎትን በሀገር ውስጥ ምርት ማሟላት ይቻላል ሲሉም ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም በሀገር ውስጥ የሚገኙ የጋርመንት እና የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪዎች የአፍ መሸፈኛ ማስክ እንዲያመርቱ በተደረገው ጥረት 81 አምራች ኢንዱስትሪዎች ተለይተው 7ቱ በቀን 217 ሺህ ማስኮችን እያመረቱ ለገበያ እያቀረቡ ሲሆን 81 ኢንዱስትሪዎች ሙሉ በሙሉ ወደ ማምረት ሲገቡ በቀን ከ5.1 ሚሊዮን በላይ ማስኮችን በማምረት ወደ ገበያ ማቅረብ ይችላሉም ብለዋል አቶ መላኩ፡፡

ቅጽ 2 ቁጥር 77 ሚያዝያ 17 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here