የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በኮቪድ 19 በተያያዘ በፌደራል መንግሥቱ ላይ ቅሬታውን ገለጸ

0
478

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከኮሮና ቫይረስ መከላከል ስራዎች ጋር በተያያዘ በፌደራል መንግስቱ ላይ ቅሬታ እንዳለው አስታወቀ።
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ ከሆኑ ክልሎች አንዱ ቢሆንም የፌደራል መንግስት ግን ትኩረት እንዳልሰጠው ተገልጿል።
የክልሉ የኮሚንኬሽን ቢሮ ኃላፊ መለሰ በየነ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት የሙቀት መለያ መሳሪያዎች እጥረት መኖሩን የተናገሩ ሲሆን እስካሁን በክልሉ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ባለመጀመሩ ከህዝብ ሰፊ ጥያቄዎችን አስነስቷል ብለዋል፡፡
ጥያቄዎች ቀርበዋል እየደረሱን የሚገኙት ምላሾች በአገር ደረጃ የሚስተዋሉ እጥረቶችን መሰረት ያደረጉ ቢሆንም የተሻሉ አማራጮችን እያፈላለግን ነው ብለዋል።
ክልሉ ለወረርሽኙ መስፋፋት ምክኒያት ይሆናሉ ያላቸውን ጉዳዮች በመለየት ጥብቅ ቁጥጥር እያደረገ መሆኑን የተናገሩት አቶ መለሰ አሁን ላይ የቫይረሱን ምርመራ በክልል ደረጃ መጀመር እንደሚገባው አቋም አለን ይላሉ፡፡
ክልሉ የጎረቤት አገራት ስደተኞች መጠለያ እና ከፍተኛ ዝውውር የሚካሄድበት አካባቢ በመሆኑ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ ምርመራ እንዲጀመር ጥያቄ ብናቀርብም ምላሹ አጥጋቢ አይደለም ብለዋል።
በኢትዮጵያ የኮቪድ 19 ቅድመ ዝግጅትና ምላሽ ምክትል አስተባባሪ ዘውዱ አሰፋ እንዳሉት ኮሮና ቫይረስን ለመመርመር የሚያግዙት የህክምና ማሽኖቹ በትክክል ተግባራዊ ሊያደርግ የሚችል ግብዓት መኖር ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል ያሉ ሲሆን የክልሎች ተጋላጭነት ግምት ውስጥ ባስገባ መንገድ የምርመራ ጣቢያዎችን ለማቋቋም እየሰራን ነው ብለዋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 77 ሚያዝያ 17 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here