የሕዳሴው ግድብ የብረታብረት ሥራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቀቀ

0
813

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት የብረታብረት ፍሬም ሥራ ሙሉ በሙሉ በመጠናቀቁን ግድቡ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ አስታወቁ። ሙሉ በሙሉ ከተጠናቀቀው የብረታ ብረት ስራ በተጨማሪ የሲቪል ሥራው 87 በመቶ፣ የኤሌክትሮ መካኒካል ሥራው ደግሞ 46 በመቶ መጠናቀቁን የሕዳሴው ግድብ ሥራ አስኪያጅ ጨምረው አስታውቀዋል።

ክፍሌ ሆሮ ምንም እንኳን በአሁኑ ወቅት የኮሮና ቫይረስ ሥጋት በዓለም ላይ ጥላውን ያጠላ ቢሆንም የሕዳሴው ግድብ ሥራ በነበረው ግለት እንደቀጠለ መሆኑን ተናግረዋል። አሁን ላይ የፕሮጀክቱ አጠቃላይ አፈጻጸም 73 በመቶ መድረሱንም ገልጸዋል፡፡

ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሠራተኞችን በመጠበቅ የሕዳሴው ግድብ ፕሮጀክት ሥራው ያለ አንዳች እንከን መቀጠል እንዲችል እየተሠራ መሆኑን የጠቆሙት ኢንጂነር ክፍሌ፣ ከግብዓት አቅርቦት ጋር በተያያዘም ችግሮች እንዳይገጥሙ ታቅዶበት እየተሠራ እንደሆነ ለኢትዮጵይ ፕሬስ ድርጅት አስታውቀዋል፡፡

ግድቡ በሚቀጥለው ዓመት መጨረሻ ላይ ኃይል ማመንጨት እንዲችል በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የገለጹት ኢንጂነር ክፍሌ፣ የውሃ ሙሊቱ በሚቀጥለው የክረምት ወራት እንደሚጀምርና እቅዱን በሚገባ ማሳካት በሚቻልበት ቁመና ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክቱ ከተጀመረ ዘጠኝ ዓመታት እንደሞሉት የሚታወቅ ሲሆን በሚቀጥለው ዓመት የውሃ ሙሌት እንደሚጀምር የኢትዮጵያ መንግስት ቁርጥ አቋም ቢኖረውም በሲስቱ አገራት መካከል ሲደረግ የኘበረው ድርድር በአሁነ ጊዜ ያለ ስምምነት መቋረጡ የሚታወስ ነው፡፡

በሦስቱ ላይኛው ተፋሰስ አገራት መካከል አሜሪካንን እና ኣለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ሰዎችን ያካተተው ድርድር ያለፍሬ መጠናቀቁ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ሲሆን በተለይም ደግሞ በኢትዮጵያ እና በግብጽ በኩል መግባባት ላይ መድረስ አለመቻሉ በሦስቱ አገራት ላይ ያለውን ድርድር ፍሬያማ ሳያደርገው ቀርቷል።

ቅጽ 2 ቁጥር 77 ሚያዝያ 17 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here