10ቱ የሴት ልጅ ግርዛት የከፋባቸው ክልሎች በቅደም ተከተል

0
2525

ምንጭ፡-ETHIOPIA National Human Development Report 2018

ሪፖርቱ እንደሚለው የሴት ልጅ ግርዛት የሚፈጸመው አሳማኝና ጠቃሚ በሆነ ምክንያት ሳይሆን ከማኅበረሰብ እድሜ ክልል ሽግግር ጋር ተያይዞ በሚተገበር ጎጂ ልማዳዊ ድረጊት ሳቢያ ነው፡፡ በሴት ላይ የሚፈጸም ግርዛት ዓለም አቀፍ የሰብኣዊ መብት ጥሰት ተደርጎ የተወሰደ መሆኑን የሚያስታውሰው ሪፖርቱ የከፋ የጠየና ችገር ይዞ እንደሚመጣም ያስገነዝባል፡፡
በኢትዮጵያ ድርጊቱ በትንሹመ ቢሆን እየቀነሰ መምጣቱንም ያክላል፡፡ ለምሳሌም እድሜያቸው ከ15 እስከ 49 ዓመት የሚገኙና ግርዛት የተፈጸመባቸው ሴቶች ቁጥር በአውሮፓዊኑ የዘመን ቀመር 2006 ከነበረበት 80 በመቶ በ2016 ወደ 65 በመቶ ዝቅ ማለቱን አንስቷል፡፡ የሁንና አሁንመ የሴት ልጅ ግርዛት የከፋባቸው ክልሎች ሲኖሩ 98 ነጥብ አምስት በመቶ ሴቶች የሚገረዙበት ሱማሌ ክልል የመጀመሪያውን ደረጃ ይዟል፡፡ በአንጻሩ ትግራይ ክልል የሴቶችን ግርዛት በመቀነስ የተሸለች ስትበል በዚያመ ቢሆን 24 ነጥብ ሁለት በመቶ ሴቶች የሚገረዙ መሆኑ ድርጊቱ ለኢትዮጵያ ገና ያልተነካ የቤት ሥራ መሆኑን አመላካች ነው፡፡

ቅጽ 1 ቁጥር 5 ታኅሣሥ 6 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here