“ግፍ ሰርቶ መደበቅ፤ ዘርፎ መንደላቀቅ አይቻልም”

0
506

ይህ አባባል ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በተለይም በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት በኩል በዜጎች ላይ ይፈፀም የነበረን የሰብኣዊ መብት ጥሰት የተመለከተ ዘጋቢ ፊልም (ዶክመንታሪ) ለሕዝቡ ይፋ በተደረገበት ማግስት ከጻፉት የተወሰደ ነው፡፡
ጠቅለላይ ሚንስትሩ ለህዝቡ ባስተላፉት የጽሑፍ መልእክታቸው አሰቃቂ ግፎች ሲፈጸሙ እደነበር በመጥቀስ ፈጻሚዎቹ “ሰውነትን” የሚለውን እሳቤ እንደማይወክሉም አንስተዋል፡፡ ወንጀለኞችንና ብሔርን መቀላቀል እንደሚስተዋልና ተገቢ አለመሆኑንም መክረዋል፡፡
“አብዲሳ አጋን፣ ጸጋዬ ገብረ መድኅህንን ወይም ታደሰ ብሩን ያፈራው የኦሮሞ ሕዝብ ጽዩፍ የሆኑ እኩያንን የማያበቅልበት፤ ጀግናው አሉላ አባ ነጋን ወይም ማኅሌታይ ያሬድን ለሀገር ያበረከተው የትግራይ ሕዝብ ታሪክ የማይረሳው በደል የፈጸሙ ወንጀለኞችን የማያፈራበት፤ እነ ቴዎድሮስን፣ በላይ ዘለቀን ወይም ገብርዬን የሸለመው አማራ ሌሎች ግፈኞችን ከውስጡ ሊያስገኝ የማይችልበት ምክንያት የለም” ም ብለዋል፡፡ በዚህም ከሁሉም ብሔር በጎ ሰው የሚወጣውን ያህል መጥፎ ሰው እንደሚበቅልም አስገንዝበዋል፡፡
“ወንጀለኞቹ ማንም ይሁኑ ማን ከየትኛውም ብሔር ገብተው ይደበቁ የትኛውም ወገን ይጩህላቸው በወንጀል እስከተጠረጠሩ ድረስ ካሉበት አድነን ለህግ ማቅረባችን ግን አይቅሬ ነው” ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ “ግፍ ሰርቶ መደበቅ፤ ዘርፎ መንደላቀቅ አይቻልም” ሲሉም አክለዋል፡፡ ይህን አገላለጽም ከባለ ሦስት ገጹ የጠቅላይ ሚንስትሩ መልዕክት በመውሰድ ብዙዎች ሳምንቱን በማኅበራዊ የመገናኘ ብዙሃን አውታሮች በተለይም ፌስ ቡክ ሲቀባበሉት ሰንብተዋል፡፡

ቅጽ 1 ቁጥር 5 ታኅሣሥ 6 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here