በኮቪድ19 ምክንያት ቀጣዩን ምርጫ ለማካሄድ አስቸጋሪ በመሆኑ መንግስት አራት የመፍትሄ አማራጮችን አቀረበ

0
463

ኢትዮጵያ ዘንድሮው ለ6ኛ ጊዜ ልታካሂደው የነበረው ብሄራዊ ምርጫ ዓለም አቀፋዊ ስጋት ሆኖ በተከሰተው የኮቪድ19 ወረርሽኝ ምክንያት በተያዘለት ጊዜ ገደብ ሊካሄድ እንደማይቻል የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ማስታወቁ ይታወሳል።

በመሆኑም “ኮቪድ19 ምርጫን ማራዘም እና የህግ አማራጮች” በሚል ርዕስ ዛሬ ሚያዚያ 21/2012 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የተለያዩ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተሳተፉበት ውይይት እያካሄደ ይገኛል።

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ምክትል አቃቤ ህግ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ዶ/ር የውይይቱን የመነሻ ሀሳቦች አቅርበው ውይቱ የቀጠለ ሲሆን በመነሻ ሃሳቡም ላይ አራት የመፍትሄ አማራጮች ተቀምጠዋል።

እነሱም
1. የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን መበተን
2. የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ
3. ህገ መንግስት ማሻሻል
4. የህገ መንግስት ትርጓሜ መጠየቅ ናቸው ተብለዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here