አምነስቲ ኢነተርናሽናል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዚህ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ወቅት የቀን ሰራተኞች እና ስራ አጥ ሰዎችን መኖሪያ ቤታቸውን ማፍረሱን አስታወቀ። አምነስቲ እንዳስታወቀው በቅርቡ መፍረሳቸው የተረጋገጠው መኖሪያዎች ወረርሽኙን ተከትሎ የዕለት ገቢያቸውን አጥተው የተቀመጡ ሰዎች ቤቶች እንደሆኑም ከነዋሪዎች ጠይቆ መረዳቱን አስታውቋል። ከዚህም ባለፈ መኖሪያ ቸው የፈረሰባቸው ሰዎች በሜዳ ላይ እንደሚገኙ እና ከሕግ አስከባሪዎች በሚደርስባቸው ወከባ እና ከዝናብ ለመጠለል በሚቀልሱት የላስቲክ መጠለያንም እንደሚያፈርሱባቸው ገልጸው በርካታ ሌሎቶችን ያለ ዕንቅልፍ እንደሚያሳልፉ አምነስቲ መረጃውን ይፋ አድርጓል።
የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ዋና ዳይሬክተር ዴፕሮስ ሙቸና አንዳስታወቁት መጠለያቸው የፈረባቸው ሰዎች ሕጻናት ልጆቻቸው ለዝናብ እና ለብርድ መዳረጋቸውን አስታውቀዋል። ነዋሪዎቹም በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከወረርሽኙ ሊተርፉበት የሚቻላቸው በቤት ውስጥ በመቀመጥ መሆኑን ተከትሎ የመኖሪያቸው መፍረስ ለወረርሽኙ ተጋላጭነታቸውን እንደሚያሰፋው አስታውቀዋል ሲል አምነስቲ በዘገባው አስታውቋል።
አምነስቲ ከቦሌ ክፍለ ከተማ ስራ ኃላፊዎች አገኘሁ ያለው መረጃ እንደሚያመለክተው በሕገ ወጥመንገድ የተገነቡ መኖሪያዎች መፍረሳቸውን ሲሆን በተቃራኒው ደግሞ መኖሪያቸው የፈረሰባቸው ግለሰቦች ከ1999 ጀምሮ ጀገበሬዎች መሬቱን በመግዛት መኖሪያውን ሰርተው መኖር እንደጀመሩ ለአምነስቲ ኢንተርናሽናል ተናግረዋል። ነዋሪዎችም የስራ ኃላፊዎች በድንገት የሚያደርጉትን የቤት ማፍረስ እንዲያቆሙ እና ከነዋሪዎች ጋር በምክክር ማድረግ እንደሚገባቸው አያይዘው ገልጸዋል።



