ኮቪድ-19ን የመከላከልና የመቆጣጠር ዝግጁነት እና ምላሽ አሰጣጥ ዙሪያ ክልሎች ያሉበት ሁኔታ የተዳሰሰበት የጉብኝት ሪፖርት ቀረበ፡፡

0
550

ከጤና ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በተውጣጡ ባለሙያዎች የተዋቀሩ የድጋፍ ቡድኖች ለክልሎች እና ለከተማ አስተዳደሮች ሲያደርጉት የነበረውን የአንድ ወር ድጋፋዊ ጉብኝ ሪፖርት ማቅረባቸው ተገለፀ፡፡

ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው የድጋፍ ቡድኖቹ በእያንዳንዱ ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች በኮቪድ-19 ዙሪያ እየተደረጉ ያሉ እንቅስቃሴዎችን በጠንካራ ጎን እና በክፍተት በመለየት በዝርዝር አቅርበዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ቡድኖቹ የተሰጣቸውን ድጋፍ የመስጠት ተልዕኮ በጥሩ ሁኔታ እያከናወኑ መሆናቸውን በመግለፅ ላበረከቱት አስተዋፅኦ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ቅንጅታዊ እንቅስቃሴዎች፣ ቅኝቶች፣ የለይቶ ማቆያዎች እና የህክምና መስጫ ማዕከላት ሁኔታ በፊት ከነበረው ጥሩ መሻሻሎችን እየታየባቸው መሆኑን የቀረቡት ሪፖርቶች እንደሚያሳዩ ገልፀዋል፡፡

እነዚህ የፌዴራል ግብረ ኃይሎች በተሰማሩባቸው ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች ከአመራሮች፣ ከባለሙያዎች እና ከሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ጋር በቅርበት በመስራት የላቀ ድጋፋዊ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ዶ/ር ደረጀ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡

ዶ/ር ደረጀ ጨምረው እንደተናገሩት የመረጃ ልውውጥ መጠናከር እንዳለበት እና አንዳንድ በቸልተኝነት የሚፈጠሩ ስህተቶች ዋጋ ሊያስከፍሉ ስለሚችሉ ሁሉም አካላት ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here