የቀድሞ የአልሸባብ መሪ በሱማልያ በቁጥጥር ስር ዋለ

0
674

የቀድሞ የአልሸባብ መሪ የሆነው ሙክታር ሮባ ባለፈው ሐመስ፤ ታህሳስ 4/ 2018 በሱማሊያ ደቡብ ምዕራብ ዞን ባይዶዋ ውስጥ በፀጥታ አስከባሪዎች እና በታጣቂዎች መሀል በነበረ የተኩስ ልውውጥ ወቅት በቁጥጥር ስር ዋለ ሲል ቢቢሲ ዘገቧል፡፡
ሙክታር አልሸባብን የመሰረቱና የመራም ሲሆን ከሁለት ወራት በፊት በምርጫ ለመወዳደር ጥያቄ አቅርበው ከሱማልያ መንግሥት ፈቃድ ባያገኝም ከአገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ጥያቄያቸው ይሁንታን አግኝቶለት ነበር።
በሚቀጥለው ሳምንት በሚደረገው ምርጫ ላይ ከሚወዳደሩና አሸንፈው ደቡባዊ ምዕራብ ዞንን ያስተዳድራሉ ተብለው ከሚጠበቁት ተወዳዳሪዎች ውስጥ አንዱ ነበሩ፡፡
ሙክታር ሮባ ከአሸባሪው አልሸባብ ጋር በነበራቸው ዝምድና የተነሳ፤ ብዙዎች በጥርጣሬ አይን ቢመለከቷቸውም አንዳንዶ ግን አልሸባብን ለመውጋት ከእሳቸው የተሻለ ሰው የለም ሲሉም ይደመጣሉ፡፡

ቅጽ 1 ቁጥር 5 ታኅሣሥ 6 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here