የኢትዮጵያ ብድር ካላት አቅም ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ መሆኑን አይ ኤም ኤፍ ው ዓለም ዐቀፍ ተቋም ባለፈው ሳምንት ባወጣው ሪፖርት ገለጸ።
የወጪ ንግድ ከሦስት ቢሊየን ዶላር ያልዘለለ መሆኑና የአገሪቱ የውጭ ምርት ፍላጎት ለሁለት ወራት እንኳን ማሟላት እንደማይችል የገለጸው ተቋሙ መንግሥት ከፍተኛ ወለድ የሚያስከፍሉ የመሠረተ ልማት ብድሮችን ከውጭ መበደር ማቆሙን አድንቋል።
ይሁን እንጂ አይ ኤም ኤፍ ለኢትዮጵያ የሰጣት ደረጃ መሠረት አገሪቷ ብድር ለመክፈል አጣብቂኝ ውስጥ እንዳለች የሚያመለክት መሆኑ የተቋሙ መረጃ ያሳያል።
እንደተቋሙ መረጃ እንደኢትዮጵያ ያሉ ከፍተኛ ብድር ጫና መደብ ውስጥ የሚካተቱ አገራት በቢሊየን ብሮች የሚጠይቁ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን በራሳቸው አቅም ካልገነቡ የብድር ወጥመድ ውስጥ ሊገቡ እንደሚችሉ ያስጠነቅቃል።
ባለፈው ዓመት መጨረሻ የወጣ ሪፖርት እንደሚያሳየው ኢትዮጵያ ከውጭ አገር አበዳሪዎች ወደ 23 ቢሊየን ብር ተበድራለች።
ቅጽ 1 ቁጥር 5 ታኅሣሥ 6 ቀን 2011