በበረከት ስምኦን እና ታደሰ ካሳ ላይ የስድስት አመት እና የስምንት አመት የእስር ውሳኔ ተላለፈ

0
729

ፍርድ ቤቱ በአቶ በረከት ስምኦን ላይ ስድስት ዓመት እና በአቶ ታደሰ ካሳ ላይ የስምንት ዓመት የእስር ውሳኔ አስተላለፈ፡፡

በአቶ በረከት ስምኦን እና በአቶ ታደሰ ካሳ ላይ የአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሥራን በማያመች መንገድ መምራት የሙስና ወንጀል ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክስ አቅርቦ ክርክር ሲያካሂድ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

ፍርድ ቤቱ የከሳሽንና የተከሳሾችን ክርክር ሲያዳምጥ ከቆየ በኋላ ሚያዝያ 26 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት መዝገቡን መርምሮ አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሰ ካሳን ጥፋተኛ ብሏል፡፡
ሚያዚያ 28 ቀን 2012 ዓ.ም የዋለው ችሎት ደግሞ በከሳሽ እና በተከሳሽ መካከል የቅጣት ውሳኔ አስተያየትን አዳምጦ የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት ለዛሬ ሚያዚያ 30 ቀን 2012 ዓ.ም መቀጠሩን የሚታወስ ነው፡፡

ዛሬ ሚያዚያ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ከሰዓት በፊት የዋለው ችሎትም በ1ኛ እና 2ኛ የክስ መዝገቦች ላይ ጥፋተኛ በተባሉት በ1ኛ ተከሳሽ አቶ በረከት ስምኦን ላይ የስድስት ዓመት እስር እና የ10 ሺህ ብር የቅጣ ውሳኔ አስተላለፏል፡፡ በ1ኛ፣ 2ኛ እና 4ኛ የክስ መዝገቦች ላይ ጥፋተኛ በተባሉት 2ኛ ተከሳሽ አቶ ታደሰ ካሳ ላይ ደግሞ የስምንት ዓመት የእስር ቅጣትና የ15 ሺህ ብር የቅጣት ውሳኔ ተበይኗል፡፡

ተከሳሾች ይግባኝ የማለት መብት እንዳላቸው የገለፀው ችሎቱ ፍርዱ በሕግ ቁጥጥር ስር ከዋሉበት ጊዜ ጀምሮ ይሰላልም ማለቱንም ከአማራ መገናኛ ብዙሀን ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here