ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በኢትዮጵያ ተጨማሪ 3 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው

0
544

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 1861 የላብራቶሪ ምርመራ 3 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ይህም በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥርን 194 አድርሶታል፡፡

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሴቶች ሲሆኑ በአዲስ አበባ የሚኖሩና እድሜያቸው ከ23-33 ዓመት መሆናቸውም ታውቋል፡፡

በተጨማሪም 2 ሰዎች በትላንትናው ዕለት ማገገማቸውን ተከትሎ በአገሪቱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 95 ደርሷል፡፡

 

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here