ከ2008 እስከ 2011 የግብር እዳ ያለባቸው ግብር ከፋዮች ወለድና ቅጣት ተነሳላቸው

0
951

የገቢዎች ሚኒስቴር ከ2008 እስከ 2011 የግብር እዳ ያለባቸውን ግብር ከፋዮች ወለድና ቅጣት ማንሳቱን አስታወቀ።
የገቢዎች ሚኒስቴር በጉዳዩ ዙሪያ በሰጠው መግለጫ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሠራተኞች ከሚሠሩበት ቦታ እንዳይቀነሱ፣ በንግዱ ላይ የሚፈጠረውን ጫና ለመቀነስ ሲባል የእዳ ስረዛው መወሰኑን ገልጸዋል። በዚህም መሰረት ከ2008 እስከ 2011 የግብር እዳ ያለባቸው ሰዎች ወለድና ቅጣት የተነሳላቸው መሆኑን አረጋግጠዋል።
በተጠቀሱት ዓመታት የግብር እዳ ያለባቸው ሁሉ የዚህ እድል ተጠቃሚ የሚሆኑት ከዛሬ ጀምሮ በአንድ ወር ውስጥ የፍሬ ግብሩን 25 በመቶ መክፈል ከቻሉ መሆኑንም አስገንዝበዋል። በአንድ ወር ውስጥ ፍሬ ግብራቸውን 25 በመቶ ክፍያ በመፈጸም ቀሪውን 75 በመቶ ደግሞ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቅ ይችላሉ ብለዋል፣ ሚኒስትሩ።
እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ይህን ማድረግ ለቻሉ ሁሉ የ10 በመቶ ከፍሬ ግብራቸው ቅናሽ ይደረግላቸዋል። ከዚህ በተጨማሪ እስከ ከ2007 የፍሬ ግብርና የወለድ ቅጣት ያለባቸው ደግሞ ሙሉ በሙሉ እዳው ተነስቶላቸዋል። የፍሬ ግብር ንብረታቸው የተያዘባቸው ንብረቱ ተመልሶላቸው ወደ ሥራ የሚገቡበት ሁኔታ እንደተመቻቸም ተናግረዋል።
ይህ የሚሆነው የተያዘው ተንቀሳቃሽና የማይንቀሳቀስ ሀብት በንግድ ወይም የቢዝነስ እንቅስቃሴ ላይ ከሆነ ነው።

ቅጽ 2 ቁጥር 79 ግንቦት 1 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here