የድሬድዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ ነገ ይመረቃል

0
645

የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ ነገ በጠቅላይ ሚንሰትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንደሚመረቅ ተገለጸ።
በቻይናው ሲቪል ኢንጅነሪነግ ኮንስትራክሽን ድርጅት የተገነባው ፓርኩ 190 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ወጪ ሆኖበታል።
ኢንዱስትሪ ፓርኩ የጨርቃ ጨርቅ ምርቶችን የምግብ ውጤቶች እና ሌሎች ምርቶችን ለውጭ ገበያ የሚያቀርብ ነው።
በ156 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ፓርኩ ለ15 ሺሕ ዜጎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥርም ተገልጿል።
ግንባታው በተጀመረበት ወቅትም| ፕሮጀክቱን የተረከበው የቻይናው ኩባንያ ሕጋዊ ስርዓትን በተከተለ መልኩ ጨረታውን አላሸነፈም በሚል ቅሬታዎች መነሳታቸው አይዘነጋም።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በመላ አገሪቱ 11 የሚሆኑ የሚሆኑ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን የገነባ ሲሆን ለግንባታም 30 ቢሊየን ብር ወጪ አድርጓል።
ባሳለፍነው ሳምንት የጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ በጠቅላይ ሚንስትሩ ተመርቆ ወደ ሥራ መግባቱ ይታወሳል።

ቅጽ 1 ቁጥር 5 ታኅሣሥ 6 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here