ከኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ከ28 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተገኘ

0
615

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለሱዳንና ጅቡቲ ካቀረበው የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ከ28 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡ ገቢው የተገኘው ከሰኔ 2010 እስከ ጥቅምት 2011 ባሉት አምስት ወራቶች ውስጥ መሆኑን የተቋሙ የማርኬቲንግና ቢዝነስ ዲቨሎፕመንት ቢሮ አስታውቋል፡፡
ከተገኘው ገቢ ውስጥ ጅቡቲ 17.5 ሚሊየን ዶላር ያህል ግዢ በመፈፀም ከፍተኛውን ድርሻ የያዘች ሲሆን ቀሪው 10.9 ሚሊየን ዶላር የተገኘው ደግሞ ከሱዳን ነው፡፡
ቢሮው አክሎም አገሪቱ ታዳሽ ኃይልን በማልማት በምሥራቅ አፍሪካ የኢኮኖሚያዊ ትስስር ለመፍጠር በስፋት እየሰራች እንደሆነ ገልጾ ለጅቡቲ እና ለሱዳን በአማካኝ ከ150 ሜጋ ዋት በላይ ለሽያጭ እያቀረበች ትገኛለች ብሏል፡፡
በቅርብ ጊዜያት ውስጥም አገሪቱ ከሶማሌ ላንድ፣ ኬንያ፣ ታንዛኒያ እና ደቡብ ሱዳን ጋር የኤሌክትሪክ ኃይል ትስስር ለመፍጠር የሁለትዮሽ ግንኙነት በማድረግ ላይ ትገኛለች። በአሁኑ ሰዓትም፤ ኢትዮጵያንና ኬንያን በኃይል ልማት ለማስተሳሰር ባለ 500 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ግንባታ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ቅጽ 1 ቁጥር 5 ታኅሣሥ 6 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here