የኦሮሚያ መንግሥት ወረርሽኙ በግብርናው ዘርፍ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ ለመቋቋም እየሠራ ነው

0
298

የኮቪድ 19 ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የግብርናው ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን ላይ የሚያሳድረውን ተጽእኖ ለመቋቋም እየተሠራ መሆኑን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ገለጸ።
በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የክልሉ መንግሥት ማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አዲሱ አረጋ፣ በዚህ ወቅት የክልሉ መንግሥት በግብርናው ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የአርሶ አደሩን ሕይወት ለውጦ ኢኮኖሚውን ለመታደግ በመካናይዜሽን የተደገፈ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።
የክልሉ መንግሥት በተለይ በገጠሩ አካባቢ ወረርሽኙን እየተከላከለ በግብርናው ዘርፍ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ በማጠናከር ቫይረሱ በኢኮኖሚ ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ እንደሚጥር ጠቁመዋል።
የግብርናውን እንቅስቃሴ ለማዘመንና በመካናይዜሽን ለማገዝ ለአርሶ አደሮች ግብዓቶችን በማሟላት ላይ ይገኛል ብለዋል። በተያዘው በጀት ዓመትም 354 ትራክተሮችን ለአርሶ አደሮቹ መከፋፈላቸውን አዲሱ አስታውሰው፣ በቅርብ ጊዜም 2 ሺሕ ትራክተሮችን ተደራሽ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑንና ወጣቱንም ወደ ግብርናው ለማስገባት እንቅስቃሴ እየተደረገ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
ከዚህ ቀደም በክልሉ አርሶ አደሩን ለመደገፍ የተሠራው ሥራ ከቃል የዘለለ አልነበረም ያሉት አዲሱ፣ ከፍተኛ የመንግሥት አካላትና ምሁራን በክልሉ ጉብኝት ማድረጋቸው ወደፊት ለሚዘጋጁ ፖሊሲና ስትራቴጂዎች ከአርሶ አደሩ ፍላጎት አንጻር ለመቃኘት ያግዛል ብለዋል።
እንደ አዲሱ ገለጻ የክልሉ መንግሥት በአምራቹና በተጠቃሚው መካከል ሆነው የአርሶ አደሩን ልፋት ዋጋ እንዳያገኝ የሚያደርጉትን ደላሎች ለማስወጣት እየሠራ ይገኛል።

ቅጽ 2 ቁጥር 82 ግንቦት 22 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here