ከተመሠረተ ስምንት ዓመታት ቢያልፍቱም በትርፍ አኳያ ውጤታማ መሆን ያልቻለው ዳሎል ኦይል በባለፈው ዓመት 6 ነጥብ ሰባት ሚሊየን ብር እንደከሰረ አስታወቀ።
ሰባተኛው ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ለማድረግ ባለፈው ቅዳሜ ተሰብሰብው ምልአተ ጉባኤ ባለመሟላቱ የተበተኑት የድርጀቱ ባለአከሲዮኖች፤ በድርጅቱ ወጤታማ አለመሆን ደስተኛ አለመሆናቸውን በተቃውሞ ገልፀዋል።
ይሁን እንጂ በደረጀ ዋለልኝ ሊቀመንበርነት የሚመራው የድርጀቱ ቦርድ ለባለአከሲዮኖች ባስቀመጠው መልዕክት የአከሲዮን ማህበሩን ህልውና ከመነሻው ሲፈታተነው የነበረው የሥራ ማስኬጃ እጥረት እየተባባሰ ቀጥሏል። ይህ በገበያ ውስጥ ካለው አስቸጋሪ ሁኔታዎች ጋር ተጣምሮ የድርጀቱ ትርፋማነት ላይ አሉታው ተፅዕኖ አሳድሯል።
በተጨማሪም በሃገሪቷ ከታየው የፖለቲካ አለመረጋጋትና የሰላም እጦት የነዳጅ ምርቶችን ለማንቀሳቀስ አዳጋች ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የድርጅቱ ገቢ እንዲቀንስ አድርጎታል።
በርግጥ፤ ዳሎል በባለፈው በጀት አመት 51 ነጥብ 3 ሚሊየን ሊትር ነዳጅ ለመሸጥ አስቦ የነበረ ቢሆንም ማሳካት የቻለው ከፊሉን ነው። አፈፃፀሙም ከባለፈው በጀት ጋር ሲነፃፀር የ17 ነጥብ 1 ሚሊየን ሊትር ልዩነት አለው። ይሁን እንጂ ከነዳጅ ውጭ ድርጅቱ በዘይትና ቅባቶች ሽያጭ ከአራት እጥፍ በላይ የሽያጭ ጭማሪ አሳይቷል።
የድርጅቱ ከነዳጅ እንዲሁም በዘይትና ቅባቶች ሽያጭ ያገኘው ገቢ አኳያ በ 187 ሚሊየን ብር ቀንሶ 434 ሚሊየን ብር ባለፈው በጀት አመት የደረሰ ሲሆን ፤ ውጪው ደግሞ በ ሁለት ሚሊየን ብር አድጎ 14 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ደርሶ ነበር።
እንደ ድርጀቱ ቦርድ ሰብሳቢ መልዕክት፤ ለድርጀቱ የሽያጭ መጠን መጠንና ገቢ መቀነስ የማህበሩ የፋይናንስ አቅም በየጊዜው እየተዳከመ መሄድ በዋነኝነት የሚጠቀስ ሲሆን የውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት በሚጠበቀው ወቅት እና መጠን የታቀዱ ዘይትና ቅባቶች በወቅቱ ሊገቡ አለመቻላቸው ዋነኛ ምክንያት ናቸው።
ለአብነት ቦርዱ፤ ከ 600 ሺህ ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ጥያቄዎችን ለተለያዩ ባንኮች አቅርቦ የተሳካለት 40 ሺህ ዶላር ብቻ መሆኑን ገልጿል።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ነዳጅ ድርጅት የዱቤ ሽያጭ አሰራሩን ጠበቅ ማድረጉ ድርጅቱ ማደያዎች ላይ ተመሳሳይ እርምጃ ለመውሰድ መገደዱ ደንበኞቹ ወደ ሌሎች ኩባንያዎች እንዲያማትሩ በማድረጉ ገቢው ላይ ከፍተኛ አሉታዎ ተፅዕኖ አድርጎበታል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ አቅራቢ ድርጀቱ ለዘገዩ ክፍያዎች ከጥቅምት 2010 ጀምሮ ከዚህ ቀደም የሚያስከፍለውን የ 10 ነጥብ 5 በመቶ የወለድ ምጣኔ ወደ 12 ነጥብ 5 በመቶ ከፍ ማድረጉ ለወጪው መጨመር እንዲሁም ለትርፉ መቀነስ ቀላል የማይባል ሚና ነበረው።
የዳሉል ቦርድ ሰብሳቢ መልዕክት መረጃ እንደሚያሳየው ድርጀቱ መክፈል የሚገባው 35 ሚሊየን ብር ውዝፍ ዕዳ በስድስት ወራት ውስጥ አጠናቆ ለመክፈል ከኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ነዳጅ ድርጅት በገባው ውል መሰረት ክፍያውን እየፈፀመ ሲሆን በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ውስጥ ያጠናቅቃል።
ወደ 53 ሚሊየን ብር ተሰብሳቢ ገንዘብ ያለው ዳሉል ኪሳራ ሲገጥመው ይህ አመት የመጀመሪያው አይደለም። በ 2009 በጀት አመት 3ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የከሰረ ሲሆን በ 2004 እና በ 2005 1 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር እና 5 ነጥብ 6 ብር ኪሳራ፤ በቅደም ተከተል ገጥሞት ነበር።
ቅጽ 1 ቁጥር 6 ታኅሣሥ 13 ቀን 2011