‹‹1ሺሕ የሚሆኑ ኩላሊት ሕሙማን አደጋ ላይ ናቸው››

0
856

በተለያየ በጎ አድራጎት ድርጅት ከዚህ ቀደም ለኩላሊት ሕሙማን ድጋፍ ይደረግ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን አሁን ባለው ሁኔታ የኩላሊት እጥበት የሚያስፈልጋቸው ነገር ግን ሕክምናውን ያልጀመሩ በአዲስ አበባ 1000 ዜጎች እንዳሉ ተገለፀ፡፡

የኩላሊት ሕሙማን በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት በዚህ ማኅበር 67 የሚሆኑ ሕሙማንን በቋሚነት እንደሚደግፍ ገልፀው፤ ከዛም በተጨማሪ በመንግስት ደግሞ 100 ለሚሆኑ ሕሙማን ለአንድ አመት የነፃ ሕክምና እንዲያገኙ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አድርገናል በዚህም በአጠቃላይ 167 ሰው ነው እየተደገፈ ነው ያለው ብለዋል፡፡

ነገር ግን ይሄ ይሁን እንጂ በአዲስ አበባ ብቻ የችግሩ ሰለባዎች ከ 1 ሺሕ በላይ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተናግረው እነዚህ ዲያሊሲስ (የኩላሊት እጥበት) ያስፈልጋቸዋል የተባሉት ናቸው ብለዋል፡፡

በተጨማሪም አሁን ላይ ለኩላሊት ሕሙማን ከባድ ስጋት የሆነው የሚሉት ሃላፊው የኮሮና ቫይረስ መከሰት እና ተጓዳኝ በሽታ ስላለባቸው ደግሞ ከባድ የስነ ልቦና ስጋት መሆኑ ነው፡፡

በዚህም ሕሙማኑ ለበሽታው ከሚያደርጉት ጥንቃቄ በላይ የኩላሊት እጥበት ለሚያከናውኑት ታማሚዎች በትንሹ በአስተያየት ሕክምናቸውን ካላገኙ ለአንድ ግዜ እጥበት እስከ 1400 ብር ያወጣሉ ያሉት የመሃበሩ ሰብሳቢ በሳምንት 3 ቀን ግዴታ ስለሆነ ደግሞ 4200 እንደሚያወጡና አገልግሎቱን የሚያገኙበት ዋጋ ላይ የተወሰነ አስተያየት እንዲደረግላቸው የማድረግ ስራ እየሠራን ነው ብለዋል፡፡

በዚህም የተወሰኑት የዋጋ ቅናሹ ላይ ዋጋ ማስተካከያውን ተቀብለውናል፤ የተወሰኑት ደግሞ የታማሚዎቹ የሶስት ወር የትራንስፖርት እየተዉላቸው ይገኛል፡፡ ቢሆንም ይሄ ግን በቂ አይደለም ብለዋል፡፡ እንደ የኩላሊት ህሙማን በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ስራ አሲኪያጅ ገለፃ ከሆነ እርሳቸው ባሉበት የበጎ አድራጎት ድርጅት ውስጥ በቋሚነት ከሚረዱት 67 ታማሚዎች ለነሱ በወር አስከ 500ሺኅ እንደሚወጣ ተናግረዋል፡፡

ከዛም በተጨማሪ ምልክቱን ከማሳየታቸው በፊት የኩላሊት ሕሙማኖች የኮሮና ቫይረስ ምርምራ ሊደረግላቸው ይገባል በማለት ከጤና ቢሮ ጋር እየሰራን ነው ‹‹ምክንያቱም በሽታ የመከላከል አቅማቸው ዝቅተኛ በመሆኑ ቫይረሱም ቢይዛቸው ቅድመ ምልክት ምንለውን ትኩሳት ማሳየት አይችሉም ›› በዛም የግድ ቀጥታ ምርመራ እንዲደረግላቸው እየተደረገ ነው ሲሉ ሰለሞን አሰፋ የኩላሊት ሕመምተኞች በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ ለአዲስ ማለዳ ተናግረተዋል፡፡

በተያያዘም ሞት በኩላሊት ይብቃ በጎ አድራጎት ድርጅት በበኩሉ እስካሁን ባለው ሁኔታ ኩላሊት ተጠቂዎች የገንዘብ ድጋፍ ሲያሥፈልጋቸው በግላቸው በመሆን የግል ገንዘብ የማሰባሰብ ሂደት የነበረ ሲሆን አሁን ግን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከጨመረ በኋላ እንዳስፈላጊው ሁኔታ ገንዘብ መሰብሰብ አለመቻላቸውን እና ንክኪው ‹‹ለነሱ ስጋት በመሆኑ ወደ ሞት እየሄዱ ነው›› ሲሉ ሞት በኩላሊት ይብቃ በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ሰብሳቢ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡

ማኅበሩ ዋና ሰብሳቢ እንደሚናገሩት ከሆነ ‹‹አግዙን ከአቅማችን በላይ ሆኗል›› የሚሉ ብዛት ቁጥር ያለቸው የኩላሊት ተጠቂዎች እንዳሉ እና በችግር ምክንያት እጥበት (ዲያሊሢስ)ማካሄድ እያለባቸው አልሄዱም በሚል የሚመጣ ጥቆማ እንዳለ ጠቅሰው ነገር ግን አሁን ተቋሙ ለእነዚህ አይነት ጥቆማዎች መልስ ለመስጠት አቅም እንደሌለው ተናግረዋል፡፡

ማኅበሩ በሚያውቀው አሁን ላይ 700 የሚደርሱ ኩላሊታቸው አገልግከሎ መስጠት ያቆመ እና እጥበት ማካሄድ (ዲያሊሢስ) ያለባቸው ታካሚዎች እናደሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡

በሕክምና ሂደቱ ውስጥ‹‹ ተገልጋይ ለመሆን የሚስፈልገው የኩላሊት እጥበቱ ብቻ የሚመስላቸው አብዛኛው ኅብረተሰቦች አሉ የሚሉት›› ዋና ሰብሳቢው ነገር ግን ከዛ ውጪ የትራንስፖርትን ጨምሮ መጠቀም ያለበት ጊዜያዊ አገልግሎቶች እና የሚዋጥ መድሃኒቶችን የግድ ለአንድ ኩላሊቱ አገልግሎት መስጠት ያቆመ ህመምተኛ ያሥፈልገዋል ብለዋል፡፡

ይህ ሲታሰብ የኮሮና ቫይረስ በራሱ ንክኪ እና ተጓዳኝ በሽታ ያለባቸውን ማኅበረሰብ የበለጠ የሚያጠቃ እንደመሆኑ ትራንስፖርት ለግል ነው መጠቀም የሚኖርባቸው፤ ሁሉም ወጪ ሲደማመር አንድ ግለሰብ ብቻውን የሚችለው አይደለም ስለዚህም እርዳታው ከግለሰብ በተጨማሪ የመንግስትም ትኩረት የግድ ያስፈልጋል ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡

በተያያዠም የአዲስ አበባ ጤና ጥበቃ ቢሮ በበኩሉ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ክፍል የኩላሊት ሕሙማንን በተመለከተ የኩላሊት እጥበት (ዲያሊሲሥ) የሚያከናውኑትን ትኩረት በመስጠት እየሰራ መሆኑን እና ከዛም በተጨማሪ መድሃኒት ተጠቃሚ የሆኑትን የረጅም ጊዜ መድሃኒት በመስጠት ወደ ህክምና ጣቢያ ሲመጡ የሚያጋጥማቸውን ንክኪ ለመቀነስ እያደረግን ነው ብሏል፡፡

ከዛም በተጨማሪ በየሆስፒታሎች ደግሞ ኩላሊት እና ተላላፊ ያልሆኑ ሕመሞች ተጎጂ የሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች ሲመጡ እነሱን ለይቶ ሕክምና መስጠት አሰራር እንዲኖር ስልጠና እየተሰጠ ነው ሲል የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ተናግሯል፡፡

ቅጽ 2 ቁጥር 83 ግንቦት 29 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here