በግንቦት ወር ብቻ ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ከ51 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ተሰብስቧል

0
837

በግንቦት ወር ብቻ ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ከ51 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ መሰብሰቡን የታላቁ የኢትዮዽያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ፅህፈት ቤት አስታወቀ።
የፅህፈት ቤቱ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ኃይሉ አብርሃም እንደገለጹት፤ በኮቪድ-19 የወረርሽኝ ወቅትም ቢሆን ህዝቡ ለግድቡ የሚያደርገውን ተሳትፎ አጠናክሮ ቀጥሏል።
ወረርሽኙ ለገቢ ማሰባሰቢያ የታቀዱ ህዝባዊ ሁነቶችን ቢያስተጓጉልም በቦንድ ግዥ እና በአጭር የፅሁፍ መልዕክት ገቢ የማሰባሰብ ስራ እየተሰራ እንደሆነም ገልጸዋል።
የታላቁ የህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን ፕሮጀክት መሆኑን ያነሱት ኃይሉ ኮሮና ወደ ኢትዮጵያ ከገባ ወዲህ ባሉት ሦስት ወራትም 180 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ድጋፍ ተሰብስቧል ብለዋል።
በዚህም መጋቢት ወር ላይ ከ49 ሚሊዮን ብር በላይ ሲሰበሰብ፣ ሚያዚያ ወር ከ79 ሚሊዮን ብር በላይ ከህዝቡ ድጋፍ ተደርጓል።
እንደ ኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተሩ ማብራሪያ በግንቦት ወር ብቻ በአጠቃላይ ከ51 ሚሊዮን 870 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ ሲሰበሰብ ከዚህ ውስጥ ከ7.5 ሚሊዮን በላይ ብር በ8100 የአጭር ፅሁፍ መልዕክት የተገኘ ነው።
ይህም የህዝቡ ተሳትፎ አሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉን ማሳያ እንደሆነም ገልጸዋል።
ህዝቡ ለግድቡ ግንባታ የሚያደርገውን አስተዋፅኦ ራሱን ከኮቪድ-19 በመጠበቅ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ኃይሉ ጥሪ አድርገዋል።
በአጠቃላይ በዓመቱ እስከ ግንቦት ወር መጨረሻ ድረስ ከ657 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ከቦንድ ሽያጭና ስጦታ፣ ከልዩ ልዩ ገቢዎች ተሰብስቧል።

ቅጽ 2 ቁጥር 84 ሠኔ 6 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here