ኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከቱሪዝም ዘርፍ ከ1 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ማጣቷ ተገለጸ

0
246

ኢትዮጲያ በያዝነው ዓመት ከቱሪዝም ዘርፉ ከ3 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ ገቢን ለማግኘት ያቀደች ቢሆንም በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የቱሪዝም እንቅስቃው በመቆሙ ከ1 ቢሊየን ዶላር በለይ ገቢ ማጣቷን የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በሚኒስቴሩ የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ተወካይ እንደገና ደሳለኝ እንዳሉን በዓመት ውስጥ ከቱሪዝም ዘርፉ ማግኘት ከነበረብን አንድ ሶስተኛውን እናጣለን ያሉ ሲሆን የሚታጣው 1 ቢሊየን ዶላር ከቱሪዝም ዘርፉ ብቻ ይሁን እንጂ ሌሎችም ከዘርፉ ጋር ተያያዥ ከሆኑ የኢኮኖሚ ዘርፎች ቀላል የማይባል ጉዳት እንደሚኖር ተናግረዋል፡፡
በጎብኝዎች ደረጃም ቢሆን 1 ሚለየን በላይ ቱሪስቶችን ለመቀበል እቅድ እንደነበረ እና በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ይህንንም ማሳካት አልቻለም ብለውናል፡፡
ኢትዮጲያ ከፍተኛውን የቱሪስት ቁጥር የምታገኘው ከመስከረም ወር ጀምሮ እስከ የካቲት ባሉት በዓላት ወቅት መሆኑን ያነሱት እንደገና በነዚህ ወራቶች ከ 541ሺ 145 ቱሪስቶች 2 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱንም ተናግረዋል፡፡
በወረርሽኙ ምክንያት የውጪ ጎብኝዎች ቁጥር ይቀዛቀዝ እንጂ አሁንም ግን ባላቸው ባህሪ የሚጎበኙ የቱሪስት መዳረሻዎች መኖራቸውን እንደገና ይናገራሉ፡፡ ከነዚህም መካከል የእምነት ተቋማት ዋነኞቹ ሲሆኑ የወረርሽኙን ስርጭት ቀድሞ ለመከላከል በሚያስችል ሁኔታ ቦታዎቹ እንደሚጎበኙ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

ቅጽ 2 ቁጥር 84 ሠኔ 6 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here