ከሩዋንዳ ድልድይ እስከ አትላስ ያለው ጎዳና በጄነራል ሰዓረ መኮንን ስም ተሰየመ

0
396

ከሩዋንዳ ድልድይ እስከ አትላስ ያለው ጎዳና በቀድሞው የኢትዮጵያ ጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ሰአረ መኮንን ስም መሰየሙ ተገለፀ፡፡

በቀጣይም በጄነራሉ ስም ሃውልት እንደሚቆምላቸው እና በስማቸው ፓርክ እንደሚሰራም ታውቋል፡፡

የጄነራል ሰዓረ መኮንን 1ኛ ዓመት ዝክረ ሰማዕታት ፕሮግራም በዛሬው እለት የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በተገኙበት ተከናውኗል፡፡

በዚህም የመታሰቢያ ስነስርዓት ላይ ከሩዋንዳ ድልድይ እስከ አትላስ ያለው ጎዳና በጄነራሉ ስም የተሰየመ ሲሆን በቀጣይም በጄነራሉ ስም ሃውልት እንደሚቆምላቸው እና በስማቸው ፓርክ እንደሚሰራም ከአዲስ ቴሌቭዥን የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here