ሚኒስቴሩ “የኔ ጉዞ” የሚል ስያሜ የተሰጠውን መተግበሪያ በመጠቀም የትራንስፖርት ክፍያን መፈጸም የሚያስችል አገልግሎት መጀመሩን አስታወቀ

0
301

የትራንስፖርት ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ይህ “የኔ ጉዞ” የተሰኘው መተግበሪያ በተንቀሳቃሽ ስልክ ላይ በመጫን በማንኛውም ሥፍራ በመሆን በሲቢኢ ብር አማካኝነት የትራንስፖርት ክፍያ መፈጸም የሚያስችል ነው ፡፡

አገልግሎቱ የሲቢኢ ብርን በመጠቀም በመናኸሪያዎች አካላዊ እርቀትን በመጠበቅ ተጠቃሚዎች ትኬት ለመቁረጥ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ የሚፈጠር አካላዊ ጥግግት ለመቀነስ የሚረዳ መሆኑም ታውቋል፡፡

አገልግሎቱን በጣም ቀላልና ምቹ በመሆኑ ይህንን ከትራንስፖርት ክፍያ አማራጮች አንዱ የሆነውን መተግበሪያ በመጠቀም ህብረተሰቡ ራሱን እና ወገኑን ከወቅቱ የኮቪድ-19 በሽታ በመጠበቅ፣ጉልበትና ገንዘቡን መቀነስ ያስችለዋል መባሉን ከትራንስፖርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here