የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች የአገሪቱን ብሄራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ በሙሉ ጊዚያቸው እየሰሩ ነው-ገዱ አንዳርጋቸው

0
317

የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ በሙሉ ጊዜያቸው እየሰሩ ካሉ ዲፕሎማቶች በተጻጻሪ በእውቀት ማነስና በአመለካከት ችግር ከቆሙለት አላማ ውጭ የሚንቀሳቀሱትን የማስተካከል ስራ እንደሚሰራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው ገለፁ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቃለ መጠይቅ “በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብና በአባይ ጉዳይ ከአገሩ ጎን የማይቆም ዲፕሎማት መኖር የለበትም” በማለት አሳስበዋል።

አያይዘውም ኢትዮጵያ በህዳሴው ግድብ ጉዳይ ድርድር በገባችበት ወቅት ማንም ሰው ከአገሩ ጎን መቆም ይጠበቅበታል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች የአገራቸውን ብሄራዊ ጥቅም በማስጠበቅ ረገድ ቀንና ሌት እየሰሩ ነው ሲሉም ገልፀዋል።

የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብና በአባይ ወንዝ ፍትሃዊ አጠቃቀም ዙሪያ ኢትዮጵያ ያላትን አቋም ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ በማሳወቅ ረገድ ሙሉ ጊዜያቸውን ሰጥተው እየሰሩ መሆኑንም አስታውቀዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here