አዲሱ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ተቋማዊ የአሰራር ለውጥ እንደሚደረግ ገለጹ

0
349

አዲሱ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አደም ፋራህ ተቋማዊ የአሰራር ለውጥ እንደሚደረግ አስታውቀዋል።

አፈ ጉባዔው ከምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች፣ ከጽ/ቤት ሃላፊ እና ዳይሬክቶሬቶች ጋር አዲሱ የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባዔ የተከበሩ ወ/ሮ እጸገነት መንግስቱ በተገኙበት ትውውቅ እና በአሰራር ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በውይይቱ የጽ/ቤቱ የሶስቱ ዓላማ ፈጻሚዎች እና የሕዝብ ግንኘነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት እስካሁን የተሰሩ ዋና ዋና የስራ አፈጻጸሞችን ላይ ውይይት ተካሂዷል።

በተጨማሪም የ2012 በጀት ዓመት እቅድ እና አፈጻጸም ምን እንደሚመስል ተገምግሟል።

ከዚህ መነሻነት የምክር ቤቱ ሁለንተናዊ አሰራር እና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ሁኔታ ላይ ውይይት ተደርጎበት አጠቃላይ የአሰራር ማሻሻያ እንደሚደረግበትም ተናግረዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here