13ኛው የኢትዮጵያ ፊልም ፌስቲቫል ይካሔዳል

0
491

13ኛው የኢትዮጵያ ፊልም ፌስቲቫል ከታኅሣሥ 15-22 ወቅታዊውን የኢትዮጵያንና የአፍሪካ ቀንድ የፖለቲካ ለውጥን መሠረት በማድረግ ‹‹ለሚመለከተው፤ ሲኒማ ፖለቲካን ይመራል›› በሚል ጭብጥ እንደሚከበር አዘጋጆቹ ለአዲስ ማለዳ በላኩት መግለጫ አስታወቁ።
የመክፈቻው ሥነ ስርዓቱ በአዲስ አበባ መስተዳድር የባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ነብዩ ባዬ በቫምዳስ ሲኒማ የሚከፈት ሲሆን በተከታታይ ቀናት የሚካሔዱት ዝግጅቶች ቫምዳስ ሲኒማን ጨምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር እና በሩሲያ ባሕል ማዕከል እንደሚካሔዱ ታውቋል።
ለስምንት ቀናት የሚቆየው ፌስቲቫል ላይ የተመረጡ የአገር ውስጥና ዓለም ዐቀፍ ፊልሞች ለዕይታ የሚቀርቡ ሲሆን የፌስቲቫሉ ማጠቃለያ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ምርጥ የኢትዮጵያ ፊልሞችን በመሸለም ይጠናቀቃል።

ቅጽ 1 ቁጥር 6 ታኅሣሥ 13 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here