10ቱ የመፈራረስ አደጋ የተደቀነባቸው አገሮች

0
403

ምንጭ፡-ዓለም አቀፍ የደስተኛነት ሪፖርት 2018 (እ.ኤ.አ)

“ፈንድ ፎር ፒስ” የተሰኘው ዓለም ዐቀፍ ተቋም በዚህ ዓመት ይፋ ያደረገው የመፈራረስ አደጋ የተደቀነባቸው አገሮች ሁኔታ አመላካች ዓመታዊ ሰነድ እንደሚጠቁመው፣ ደቡብ ሱዳን ከፍተኛ የመፈራረስ አደጋ ከተጋረጠባቸው አገራት ቀዳሚ ነች። አውሮፓዊቷ ዴንማርክ በጣም አነስተኛ የመፈራረስ አደጋ የተጋረጠባት አገር በመሆን 178ኛ ደረጃን ይዛለች።
ሰነዱ የመፍረስ አደጋ የተደቀነበት ደረጃ ሲያወጣ የአገራቱን የደኅንነት ስጋት፣ የመንግሥት ቅቡልነትና መሠረታዊ ተግባራትን የማከናወን አቅም፣ የኢንቨስትመንት ከባቢ፣ ኢኮኖሚ እና ኅብረተሰቡ ውስጥ ያለውን ክፍፍል ተመልክቷል።
በዚህ አኳያ፤ 15ኛ ደረጃ የያዘችው ኢትዮጵያ ያለፉትን ዓመታት እጅግ የከፋ የመፈራረስ አደጋ የተጋረጠባት አገር ሆና መዝለቋን ሪፖርቱ ያሳያል።
በተጨማሪም የመፍረስ ሥጋት ውስጥ ያሉ አገራት በአብዛኛው በሚቃረኑ ማንነቶችና በቡድን የተከፋፈሉ መሆናቸውን ሪፖርቱ ያመለክታል፡፡

ቅጽ 1 ቁጥር 6 ታኅሣሥ 13 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here