ፓርቲዎቹ ይዋሃዳሉ ተባለ

0
458

ኢዴፓ፣ ሠማያዊ ፓርቲ፣ አርበኞች ግንቦት ሰባትና የቀድሞው የአንድነት አባላት እስከ መጋቢት 30/2011 ሙሉ በሙሉ እንደሚዋሃዱ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) አስታወቀ፡፡
በአሁኑ ወቅት ከወረዳ ጀምሮ ያሉ የተለያዩ መዋቅሮችን ከፓርቲዎቹ አመራሮች ጋር በመሆን እየሰሩባቸው እንደሆነ የኢዴፓ ፕሬዘዳንት ጫኔ ከበደ (ዶ/ር )ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።
የሠማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር የሺዋስ አሰፋ በበኩላቸው ሠማያዊ በርዕዮት ዓለም ከሚመስሉት የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ተዋህዶ ለመሥራት ፍላጎት እንዳለው በተደጋጋሚ ሲናገሩ እንደነበር ይታወሳል፡፡ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ጸኃፊ አንዳርጋቸው ጽጌም ከአዲስ ማለዳ ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስ ንቅናቄው ከሚመስሉት ጋር ሊዋሃድ እንደሚችልና ለዚህም እየሰራ እነደሆነ ተናግረው ነበር፡፡

ቅጽ 1 ቁጥር 6 ታኅሣሥ 13 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here