በመቀሌ ዙርያ የእንደርታ ወረዳ አስተዳደር ከ400 በላይ ቤቶችን አፈረሰ

Views: 494

በመቀሌ ዙርያ የእንደርታ ወረዳ አስተዳደር ከ400 በላይ “ሕገ-ወጥ ናቸው” ያላቸውን ቤቶች ማፍረሱ ታወቀ። “ከኻያ ዓመት በፊትም ሆነ በቅርቡ የተሠሩ ቤቶች በአንድ ላይ መፍረሳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

የእንደርታ አካባቢ ነዋሪዎች ለቢቢሲ አማርኛ እንደገለጹት፣ የወረዳው አስተዳደር በልዩ ኀይል እና በፖሊስ ታጅቦ ነው እርምጃውን የወሰደው። ሁኔታውን የተቃወሙ እና ፎቶ ያነሱ ሰዎችም መታሰራቸውንም ነዋሪዎቹ ገልፀዋል።

ስለጉዳዩ መረጃ እስክናቀርብ እንኳን ጊዜ አልተሰጠንም ያሉት ነዋሪዎቹ፣ “ይፈርሳል? አይፈርስም?” ስለሚለው ነገር እንኳን በቂ መረጃ እንዳልነበራቸው ተናግረዋል። በምሽት ልዩ ኀይል እና ፖሊስ ዶዘር ይዘው መጥተው እቃዎቻችሁን አውጡ በማለት እንዳፈረሱባቸው ያወሳሉ። ቤታቸው ከፈረሰባቸው አንዳንዶቹ ሜዳ ላይ ድንኳን ሠርተው ተጠልለው እንደሚገኙም ታውቋል።

ከአማራ ክልል ተፈናቅለው የመጡ አንዳንድ ሰዎች በዚህ አካባቢ መሬት ገዝተው ይኖሩ እንደነበርና እራሳቸውን በማደራጀት ላይ ሳሉ ይህ ነገር መፈጠሩን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 37 ሐምሌ 13 2011

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com