በመክር ቤት አባላት አጩነታቸው ላይ ጥያቄና ትችት የተሰነዘረባቸው የቀድሞ የሕግና ፍትሕ አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ገ/እግዚአብሔር አርአያ ከፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ አባላት ከእጩነት ራሳቸውን አገለሉ።
የፍትሕ ስርአቱ በተጠናከረ መንገድ እንዲቀጥልና ከዚህ ቀደም የታዩ ክፍተቶችን ለማረም በሚል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለፌደራል ዳኞች ጉባኤ አባላት ጴጥሮስ ወ/ሰንበትን፣ ሰናይት አንዳርጌን እና ገ/እግዚአብሔር አርአያን በእጩነት አቅርቦ ነበር፡፡
ምክር ቤቱም የጴጥሮስ እና ሰናይትን አባልነት በአብላጫ ድምፅ አጽድቆ ገ/እግዚአብሔር ‹‹የሕግ ሙያ የሌላቸው እና ከዚህ ቀደም በነበሩበት ቋሚ ኮሚቴ ክፍተቶች እንደነበሩ›› በመጥቀስ እንደገና እንዲታዩ ሲል ጠይቋል፡፡
ገ/እግዚአብሔር የሕግና ፍትህ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆነው ባገለገሉበት ወቅት የዳኞች የስነ ምግባርና የዜጎች የሰብኣዊ መብቶች ላይ በርካታ ችግሮች ነበሩ ያሉት የሕዝብ እንደራሴዎች በእጩው ተገቢነት ላይ ጥያቄዎችን ሰንዝረዋል።በምክር ቤቱ የተነሳው ሐሳብ እውነት መሆኑን የገለጹት ገ/እግዚአብሔር የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ አባል መሆን እንደማይፈልጉ ጠቅሰው ራሳቸውን ከእጩነት አግልለዋል፡፡ ምክር ቤቱም በገ/እግዚአብሔር ምትክ ሌላ እጩ እንደሚያቀርብ አሳውቋል፡፡
ቅጽ 1 ቁጥር 6 ታኅሣሥ 13 ቀን 2011