90 በመቶ የሚሆኑት ሚኒስትሮች ሀብታቸውን ማስመዘግባቸው ተገለጸ

0
1262

የፌደራል ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ቀደም ሲል ባወጣው የ2012 በጀት ዓመት የመንግስት ባለስልጣናት የሀብት ምዝገባ ቀነ ገድብ 90 በመቶ የሚሆኑ የፌደራል ሚኒሰቴር መስሪያ ቤት ባለስልጣናት በተሰጠው ቀነ ገደብ ማስመዝገባቸውን ኮሚሽኑ ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ፡፡

በተቀመጠው ጊዜ ገደብ ሀብታቸውን ካስመዘገቡ የፌደራል መስሪያ ቤት አመራሮች (ሚኒስቴሮች) ዋና ዋና የሚባሉት ሀብታቸወን ማስመዝገባቸውን ኮሚሽኑ ለአዲስ ማለዳ አስታውቋል፡፡

በአንጻሩ የፌደራል የስነ ምግባርና የፀረሙስና ኮሚሽን የፌደራል፣ የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር አመራሮች እንዲሁም የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኃላፊዎች እስከ ሰኔ 30/2012 ድረስ ሀብታቸውን እንዲያስመዘግቡ ቀነ ገደብ በሰጠው በሰረት 10 በመቶ ያክሉ የሚኒስቴር መስሪያ ቤት ኃላፊዎች (ሚኒስቴሮች) በተሰጠው ጊዜ ገደብ ሀብታቸውን አለማስመዝገባቸውን የፌደራል ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የሀብት ምዝገባና ማሳወቅ ዳይሬክተር መስፍን በላይነህ ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል።

ዳይሬክትሩ ለአዲስ ማለዳ እንዳስረዱት ኮሚሽኑ በሰጠው ጊዜ ገደብ ሀብታቸውን ላላስመዘገቡ ሚኒስቴሮች በተደጋጋሚ ደብዳቤ እንደተፃፈላቸው እና በቅርብ ሰዎችና በምክትል ኃላፊዎቻቸው በኩል ሀብታቸውን እንዲያስመዘግቡ ተነግሯቸው እስካሁን እንዳላስመዘገቡ ታውቋል፡፡ ኮሚሽኑ በአዲስ አበባ ሰኔ ወር ላይ የተፈጠረውን ችግር ምክንያት በማድረግ ሚኒስቴር ሀላፊዎቹ ሀብታቸውን አስከ ሀምሌ 30/2012 ድረስ እንዲያስመዘግቡ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡

ኮሚሽኑ በሰጠው ተጨማሪ የሀብት ማስመዝገብ የጊዜ ገደብ ሀብታቸወን ያላስመዘገቡ ሚኒስቴሮች ሀብታቸወን የማያሰመዘግቡ ከሆነ፣ ስማቸውን በመጥቀስ ወደ ሕግ ተቋማት አሳልፎ እንደሚሰጥ ዳይሬክተሩ አሳስበዋል፡፡ በተጨማሪም ሀብታቸውን ለማሳወቅ ፈቃደኛ ያልሆኑ ኃላፊዎችን ስም ዝርዝር ኮሚሽኑ ከሀምሌ ሰላሳ ብኃላ ለህዝብና ለሚዲያ ይፋ እንደሚደርግ መስፍን ተናግረዋል፡፡

የባለስልጣናቱ የሀብት ምዘገባ የተከናወነው የትዳር አጋራቸውን እና እድሜቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ልጆችን ያካተተ መሆኑን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡ ነገር ግን የሀብት ምዝገባው እድሚያቸው ከ18 ዓመት በላይ ሆኑ የባለስልጣናት ልጆች ስም የተመዘገበ ሀብትን አይመለክትም ተብሏል፡፡

የመንግስት ባለስልጣነት ሀብት ምዝገባ እስከ ወረዳ ድርስ በመንግስት የሚሾሙ ሀላፊዎች ያካትታልም ተብሏል፡፡ በአጠቃላይ በአገር ደረጃ እስካሁን ከ500 ሺህ በላይ የመንግስት ላኃፊዎችን የሀብት ምዝገባ መከናወኑን የኮሚሽኑ የሀብት ምዝገባና ማሳወቅ ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል፡፡ ከዚህ ውስጥ 220 ሺህ ያክሉ ከፌደራል መንግስት መስሪያ ቤቶች፣ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ከድሬድዋ ከተማ አስተዳደር መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በአገር አቀፍ ደረጃ ከተከናወነው የመንግሰት ኃላፊዎች የሀበት ምዝገባ ውስጥ የአፋርና የሶማሊ ክልል አለመካተቱን መስፍን ለአዲስ ጠቁመዋል፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያ ኹለቱ ክልሎች በ2002 የወጣውን የሀብት ማሳወቅ እና ማስመዝገብ ሥርዓት አዋጅ ባለማጽደቃቸው መሆኑን መስፍል አክለው ገልጸዋል፡፡ ኹለቱ ክልሎች አዋጁን ለማጸቅ በሂደት ላይ መሆናቸውም ተጠቁሟል፡፡

በሌላ በኩል የፌደራል ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የባለስልጣናትን ሀብት በኦንላይን በይፋ የሚያሳይ ስርዓት ማዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡ ኮሚሽኑ ያዘጋጀው ስርዓት ዘመናዊ እንደሆነና ማንኛውም ሰው የሚፈልገውን መረጃ አስመርጦ ሚሰጥ ነው ተብሏል፡፡

ይህን ስርዓት ተግባራዊ ለመድረግ የሚስችል የቀደመውን አዋጅ በማሻሻል ኮሚሽኑ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ረቂቅ አዋጅ ማቅረቡን ዳይሬክተሩ አመላክተዋል፡፡ የማሻሻያው ዋና አላማ የመንግስት ባለስልጣናትን ሀብት ለማወቅ የሚፈልግ ሰው በፅሑፍ ጥያቄ ማቅረብ አለበት የሚለውን አዋጅ በማሻሻል ማንኛውም ሰው ወደ ኮሚሽኑ መምጣት ሳይጠበቅበት የሚፈልገውን መረጃ ባለበት መግኘት ለማስቻል መሆኑን መስፍን ጠቁመዋል፡፡

ቅጽ 2 ቁጥር 90 ሐምሌ 18 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here