ፈሊንት ስቶን ሆምስ በታንዛንያ የሪል ስቴት ዘርፍ ላይ ሊሰማራ ነው

0
1092

ፈሊንት ስቶን ሆምስ በታንዛንያ ዳሬ ሠላም 14 ሺሕ ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፉ አራት አፓርትመንት ሕንፃዎችን ለመገንባት በአገሪቱ ከሚገኙ ባለሀብቶች ጋር ስምምነት ላይ መድረሱ ታውቃል።
ኢትዮጵያዊው የቤት አልሚ ድርጅት አሁን ላይ ግንባታውን ለመጀመር የሚስችለውን ንድፉን (ዲዛይን) አጠናቆ ለታንዛንያ ቤቶች ኮርፖሬሽን ሊያስርክብ መሆኑን የድርጅቱ ምክትል ሥራ አስከያጅ ብሩክ ሽመልስ ለአዲስ ማልዳ ገልጸዋል።
በተጨማሪም በታንዛንያ ካልሳሳ ግዛት በስድስት ሺሕ 600 ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፉ አፓርትመንቶችን ለመገንባት ስምምንት ላይ ደርሷል።
ፍሊንት ስቶን ሆምስ ሪል ስቴት በፀደቀ ይሁኔ የተመሠረተ ሲሆን እስካሁን ከ20 ሺሕ በላይ ቪላና አፓርታማ ሰርቶ ለተጠቃሚዎች እንዳስረከበ መረጃዎች ያሳያሉ።

ቅጽ 1 ቁጥር 6 ታኅሣሥ 13 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here