ዘመን ባንክ ኹለተኛ ዙር ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሔደ

0
997

ዘመን ባንክ በአገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በመደገፍ ለኹለተኛ ዙር ችግኝ ተከላ ዛሬ ነሐሴ 2/2012 አካሔደ።
ከኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማኅበር ጋር በመተባበር በእንጦጦ የተፈጥሮ ፓርክ የችግኝ ተከላ ያካሔደው ባንኩ በዕለቱ የባንኩ ከፍተኛ አመራሮች እና የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ኢንጅነር አበበ ድንቁም ተሳታፊ እንደነበሩ ባንኩ ለአዲስ ማለዳ በላከው መግለጫ ለማወቅ ተችሏል። ከችግኝ ተከላው መርሃ ግብር ላይ ከመሳተፍም ባለፈ ባንኩ ለኮቪድ 19 ካደረገው ድጋፍ ባለፈም ለጤና ሚኒስቴር ሰራተኞች ድጋፍ የሚውል ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ድጋፍ ማበርከቱም ታውቋል። ባንኩ ከዚህ ቀደም መጋቢት 29/2012 የ 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለኮቪድ 19 መከላከል ብሔራዊ ኮሚቴ ገቢ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን ወረርሽኙን ለመከላከል ለተሰማሩ የጠየና ባለሙያዎች ድጋፍ የሚውልም የ1 ሚሊዮን ብር ድጋፍም በማድረግ የሕዝብ አነኝታነቱን ያስመሰከረ ባንክ ነው።
ዘመን ባንክ በተለየ የባንክ አሰራር ፈር ቀዳጅ ዮነ ባንክ ሲሆን ባንኩ በ2012 በጀት ዓመት ባሳየው ጠንካራ አፈጻጸም ከ 1 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ ማስመዝገቡም ታውቋል።
ቅጽ 2 ቁጥር 92 ነሐሴ 2 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here