‹የሕዝብ አስተያየት› እና ተዛማጅ ጽንሰ ሐሳቦች የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ በቃ

0
527

በአድማሱ ጣሰው (ዶ/ር) የተጻፈ ‹የሕዝብ አስተያየት› እና ተዛማጅ ጽንሰ ሐሳቦች የተሰኘ መጽሐፍ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ የመጻሕፍቱን ገበያ ተቀላቅሏል።
በመጽሐፉ ዙሪያ የተለያዩ ምሁራን አስተያየታቸውን ያሰፈሩ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባዮሎጂ ኢመርተስ ፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ በበኩላቸው፣ መጽሐፉ ከማስተማሪያ መጻሕፍት ጋር በአባሪነት ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል ነው ብለዋል። ይልቁንም ለኮምዩኒኬሽን፣ የፖለቲካ ሳይንስ፣ ማኅበረሰብ ጥናትና ሥነልቦና ዘርፎች ከፍተኛ ጥቅም ያለው ነው ሲሉም ዕይታቸውን አካፍለዋል።

ንጉሤ ተፈራ (ዶ/ር) በተመሳሳይ በመጽሐፉ ዙሪያ ዕይታቸውን ያካፈሉ ሲሆን፣ የሕዝብ አስተያየት ምንነትና መገለጫዎች እንደ ኅብረተሰብ ባህል፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ የእድገት ደረጃ አልፎም መንግሥት እደሚከተለው የፖለቲካ አቅጣጫና ርዕዮት ዓለም ሊወሰን ይችላል ይላሉ።

የሕዝብ አስተያየት ገንቢ የሚሆነውን ያህል አጥፊ ሊሆን ይችላል የሚሉት ንጉሤ፣ መሠረቱ ግን አስተማማኝ የሚሆነው ሐሳብን በነጻነት መግለጽን የመሳሰሉ ዴሞክራሲያዊ መብቶች ተግባራዊ መሆን በሚችሉበት አውድ ነው ብለዋል።

መጽሐፉ በ188 ገጾች የተቀነበበ ሲሆን በተለያዩ የመጻሕፍት መደብር ለአንባብያን ቀርቧል።

ቅጽ 2 ቁጥር 93 ነሐሴ 9 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here