10ቱ ከፍተኛ ሰላምና ነፃነት ያላቸው ለሥራ ምቹ የሆኑ አገራት

0
550

ምንጭ፡ – ግሎባል ፋይናንስ (2020)

ግሎባል ፋይናንስ በ2020 ነሐሴ ወር ባወጣው ዘገባ፣ በዓለም ላይ ሀብት ለማፍራት የሚቻልባቸው እንዲሁም ሰላም የሰፈነባቸውና ነጻነት የሚገኝባቸው አገራት በማለት በዐሰርቱ ዝርዝር ለይቶ አስቀምጧል።

የአንድ አገር የእድገት ሁነኛ ምንጭ የሰላም ሁኔታ መጠበቁ እንደሆነ ይታመናል። እናም አንድ ሰው ካለበት አገር ወደ ሌላ አገር ለሥራም ይሁን ለመኖር እንቅሰቃሴ ሲያደርግ ቀድሞ የሚታየው የግለሰብ ጥበቃ (ለችግር ተጋላጭ ነው ወይ) የሚለው ሲሆን፣ ቀጣዩ ደግሞ ሰላም ነው ወይስ ሁከት አለው የሚለው ነው።

ከዛም ባለፈ የተፈጥሮ አደጋዎች የመከሰት እድል ይቃኛል። እነዚህን ሁሉ ነጥቦች መሠረት አድርጎና አካትቶ ግሎባል ፋይናንስ እንዳወጣው ሪፖርት ለአደጋ ተጋላጭ (ሰላምና መረጋጋት ያለባቸው አገራት) ብሎ ካወጣቸው ውስጥ አይስላንድ አንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

እነዚህ አገራት በሰው ሠራሽም ሆነ የተፈጥሮ ረብሻና አደጋ ያልተጋለጡ፣ ሰላማቸው የተጠበቀ እንዲሁም ለሥራ ምቹ የሆኑ አገራት መሆናቸውን ዘገባው አካቷል።

ቅጽ 2 ቁጥር 95 ነሐሴ 23 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here