በአዲስ አበባ የሚገኙ ባንኮች ተማሪዎችን ከማገዝ ጀምሮ የከተማዋን ልማት ለመደገፍ ቃል ገቡ

0
912

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመጪው የትምህርት ዘመን ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ አቅርቦት ድጋፍን በተመለከተ ከተለያዩ የባንክ የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አያደረጉ ሲሆን፤ በዚህም ባንኮች የተጀመረውን ከተማዋን ልማት እና ተማሪዎችንም ለማገዝ ቃል መግባታቸውን አስታውቀዋል።

የባንክ ሀላፊዎቹ ተማሪዎችን ለመደገፍ ባለፉት ዓመታት የከተማ አስተዳደሩን ጥሪ በመቀበል ከደብተር ጀምሮ ሌሎች ድጋፎችን ሲያደርጉ መቆየታቸውን ገልጸው በቀጣይ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል ።

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው የከተማዋን ኢኮኖሚ በማንቀሳቀስ እና ገጽታዋን በመቀየር ረገድ የግል እና የመንግስት ባንኮች እንዲሁም የፋይናንስ ተቋማት ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ እንደሆነ ተናግረዋል።
የተማሪዎች ምገባን ጨምሮ ሌሎች የተጀመሩ ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎችን እንዲደግፉም አዳነች አቤቤ ጥሪ አቅርበዋል ።

ቅጽ 2 ቁጥር 96 ነሐሴ 30 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here