ግማሽ ቢሊዮን ብር የፈጀው ሆቴል ተመረቀ

0
366

የኃይሌ ሆቴሎችና ሪዞርቶች ድርጅት በ500 ሚሊዮን ብር በአዳማ ከተማ ያስገነባው 7ኛው የኃይሌ ሪዞርት ዛሬ ተመርቋል።
በሪዞርቱ የምርቃት ስነ ስርዓት ላይ ሻለቃ ኃይሌን ጨምሮ የሪዞርቱ የስራ ኃላፊዎች መግለጫ ሰጥተዋል።

ዛሬ የተመረቀው ሪዞርት ሰፋፊና ምቹ የመመገቢያና የስብሰባ አዳራሾች ጨምሮ 106 የእንግዳ ማረፊያ ክፍሎች፣ የስፖርት ማዘወትሪያ ስፍራዎች፣ የመዋኛ ገንዳዎች እና ሌሎችንም መሰረተ ልማቶችን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።

በአዳማ የተገነባው ሰባተኛው ሪዞርት በ500 ሚሊየን ወይም በግማሽ ቢሊየን ብር ወጪ ተገነባ መሆኑን ኃይሌ በመግለጫው ገልጿል።
ከዚያም ባለፈ 300 ለሚሆኑ ዜጎችም የስራ እድል መፍጠሩን ተናግሯል።

ሪዞርቱ በግንባታም ሆነ በአገልግሎቱ ከሌሎች ሪዞርቶች ለየት ባለ መልኩ መቅረቡን የተናገረው ሻለቃ ሀይሌ ባለ 4 እና 5 ኮኮብ ደረጃን የሚያሟሉ አገልግሎቶችን እንደሚሠጥ ገልጿል።
ግንባታውንም ለማጠናቀቅ ሁለት ዓመታትን የፈጀ ሲሆን በአዲሱ ዓመት እየተገነቡ ያሉ ሶስት ሪዞርቶች እንደሚጠናቀቁ ገልጿል።

ኃይሌ ገብረስላሴ በቅርቡ በሰሜን ጎንደር ዞን በደምቢያ ወረዳ ጎርጎራ ከተማ ተጨማሪ የቱሪስት መዳረሻ ለመገንባት ውሳኔ ላይ መድረሱ የሚታወስ ሲሆን ይህም የድርጅቱን ሆቴሌች ሰንሰለት ቅርንጫፎች ብዛት ከፍ እንደሚያደርገው ይጠበቃል።

ቅጽ 2 ቁጥር 96 ነሐሴ 30 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here