በኦሮሚያ ክልል ቻይንኛ፣ ፈረንሳይኛ እና ጀርመንኛ ቋንቋዎችን ትምህርት ሊጀመር ነው ተባለ

0
321

የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ቻይንኛን ጨምሮ በፈረንሳይ እና በጀርመንኛ ቋንቋዎችን ተማሪዎቹ ማስተማር ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ።
ቢሮው አንዳስታወቀው በ2014 ተግባራዊ የሚደረገው አዲሱ ፍኖተ ካርታ ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው አንዲማሩ በሚያዘው መልኩ ክልሉ ከሚያስተምረው ኦሮምኛና አማርኛ ቋንቋ በተጨማሪ የሶማሊኛ ቋንቋን አካቶ ሊያስተምር ነው፡፡

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ቶላ በሪሶ(ዶ/ር) ሶማሊ ክልል ከኦሮሚያ ጋር የምትዋሰን በመሆኑ ተማሪዎችን በሶማሊኛ ቋንቋ ለማስተማር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን መናገራቸውን ኢትዮ ኤፍ ኤም ዘግቧል፡፡

ተማሪዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪዎች እንዲሆኑ በሚል ደግሞ ሶስት ዓለም አቀፍ ቋንቋዎችን ማለትም የቻይና፣የጀርመንና ፈረንሳይኛ ቋንቋን በክልሉ ተማሪዎች ለማስተማር መታቀዱንና ለዚህም ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ነግረውናል፡፡

ሀገር በቀል እውቀቶችን አካቶ ከማስተማር አንፃርም ክልሉ የገዳ ስረዓት በትምህርት ስርዓት ውስጥ እንዲካተት ማድረጉንና አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን የነገሩን ዶክተር ቶላ በያዝነው ዓመትም በትምህርት ስርዓት ውስጥ ተካቶ ይሰጣል ተብሏል፡፡

ቅጽ 2 ቁጥር 99 መስከረም 16 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here