ኢትዮጵያና የዓለም ባንክ ለግብርና ዘርፍ እድገት የ80 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ

0
1460

ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ የግብርናውን ዘርፍ እድገት ለመደገፍ የ80 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ስምምነት ተፈራርመዋል።
የድጋፉን ስምምነቱን የተፈራረሙት የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ እና የአለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ፣ የሱዳንና ደቡብ ሱዳን ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን ናቸው።
የአለም ባንክ ስራ አስፈፃሚ ቦርድ የባንኩ አንድ አካል የሆነው አለም አቀፉ የልማት ማህበር ለኢትዮጵያ 80 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ እንዲያደረግ ባሳለፍነው መስከረም 5 /2013 ውሳኔ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል። የድጋፍ ስምምነቱም የባንኩ የስራ አስፈፃሚ ቦርድ ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ የተካሄደ ነው።
የገንዘብ ድጋፍ ስምምነት የሚያተኩረው ግብርና ሚኒስቴር በሁለተኛው የግብርና ዕድገት ፕሮግራም በተለያዩ ክልሎች የአርሶ አደሮች ኑሮ እንዲያሻሻል የግብርና ምርትና ምርታማነት የሚያሳድጉ፣ የተጨማሪ ገቢ ማገኘት የሚያስችላቸውና የግብርና ምርት ዕሴት ሰንሰለት እንዲጎለብት እየተገበረ ለነበሩ ፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያ ላይ ነው።
እንዲሁም የአነስተኛ አርሶ አደሮች የግብርና ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የሚያግዝ እንደሆነ መገለፁን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

ቅጽ 2 ቁጥር 99 መስከረም 16 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here