የንፁህ መጠጥ ውሃ አሁን ካለበት 66 በመቶ ሙሉ በሙሉ ተደራሽ ለማድረግ ታቅዷል

0
800

በቀጣይነት ያለው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማረጋገጥ በመጠጥ ውሃ፣ መስኖ ልማትና ኢነርጂ ላይ በሙሉ አቅሙ እየሰራ መሆኑን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገለጸ።
ሚኒስቴሩ ለሚቀጥሉት አስር ዓመታት የተያዘው ዕቅዱን ለማዳበር ከባለድርሻ አካላት ጋር በገመገመበት ወቅት ሲሆን በግምገማውም የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶከተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ እንደገለፁት የማህበራዊና ኢኮኖሚ ልማት ቀጣይነት ለማረጋገጥ በተለይ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት፣ መስኖ፣ ኢነርጅና የንፁህ መጠጥ ውሃ ወሳኝ ናቸው። በዚህም የንፁህ መጠጥ ውሃ አሁን ካለበት 66 በመቶ ሙሉ በሙሉ ተደራሽ ለማድረግ ታቅዷል።
የአርሶ አደሩና የአርብቶ አደሩን ኑሮ ከማሻሻል ባለፈ ከውጭ የሚገባውን ስንዴን በሀገር ውስጥ መተካትና ለግዥ የሚወጣውን የውጭ ምንዛሬን ማስቀረት የዕቅዱ አካል እንደሆነም ተናግረዋል።
የኃይል አቅርቦት ላይ ባለፉት አምስት ዓመታት የነበረው የልማት ሂደት የተጓተተ ከመሆኑም ባለፈ ሀገራዊ ሽፋኑ 45 በመቶ ብቻ መሆኑን ጠቅሰዋል። በዚህ ሁኔታ የተጀመረውን ልማት በሚፈልገው መልኩ ማስቀጠል አይቻልም ብለዋል። ዕቅዱ ከሀገራዊ የመልማት ፍላጎት ጋር የተቃኘ መሆን እንዳለበት አመልክተዋል።
ባለፉት አምስት ዓመታት ከ21 ሚሊዮን በላይ ህዝብ በገጠርና በከተማ የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ሆኗል ያሉት ሚኒስትሩ፣ በተመሳሳይ ከ4ሺህ 400 ሜጋ ዋት በላይ ኃይል የማመንጨት አቅም መፈጠሩን አውስተዋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 99 መስከረም 16 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here