መክሊት ሀደሮ በአዲስ አበባ የሙዚቃ ዝግጅቷን ታቀርባለች

0
626

ታዋቂዋ ኢትዮጵያዊ አሜሪካዊት ድምፃዊት መክሊት ሀደሮ ከሙሉ ባንዷ ጋር ከአሜሪካ፣ ሳንፍራንሲስኮ አዲስ አበባ በመምጣት የሙዚቃ ዝግጅቷን ጥር 3 አዲስ አባበ አሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴስ የፈረንሳይ ባሕል እንደምታቀርብ ታውቋል።
የመጨረሻ አልበሟ የሆነውን ‹When the People Move, the Music Moves Too› በ‹ሲክስ ዲግሪስ ሪከርድስ› አሳታሚነት ከዓመት በፊት ለአድማጮች ያቀረበችው መክሊት፥ ሙዚቃውን የሠራላት የባለብዙ ግራሚ ተሸለሚውና የታዋቂዎቹን አዴልና ጆን ሌጀንድን አልበሞች በመሥራት የሚታወቀው ዳኒስ ዊሊስ ነው። አልበሙ አስራ አንድ ሙዚቃዎች የተካተቱበት ሲሆን መነሻ ሐሳቦቹን ከታዋቂው የኢትዮ ጃዝ አባት ሙላቱ አስታጥቄ ጋር ያደረገቻቸው ንግግሮች መሠረት ያደረጉ እንደሆኑ ታውቋል።
በልዩ መድረክ አቀራረቧ ቀልብ ሳቢ የሆነችው መክሊት ከዚህ ቀደም ኢትዮ ጃዝ ስልት ያለውን ሙዚቃዋን በአዲስ አበባ፣ በሳን ፍራንሲስኮ፣ ሮም፣ ካይሮና በሌሎች ቦታዎች ማቅረቧ ታውቋል።
ከድምፃዊነት ባሻገር የሙዚቃ ግጥም ደራሲና ሙዚቃ አቀናባሪ የሆነችው መክሊት የአዲስ አባባ ላይ የመጨረሻ የሙዚቃ ዝግጅቷ ከሰባት ዓመታት በፊት ማቅረቧ ታውቋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 7 ታኅሣሥ 20 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here