10ቱ በተፈጥሮ አደጋዎች የተፈናቀሉ አገራት ሕዝቦች

0
542

ምንጭ፡-የዓለም ተፈናቃዮች መቆጣጠሪያ ማዕከል

በባለፈው የአውሮፓውያን ዓመት በተለያዩ አገራት በተከሰተ ተፈጥሮዋዊ አደጋዎች ከ18 ነጥብ ስምንት ሚሊየን በላይ ሰዎች ከሚኖሩበት ቀዬ ተፈናቅለዋል። በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የተፈናቀሉት ከፍተኛውን ድርሻ ይዘዋል። በሌላ በኩል፤ በጎርፍ ምክንያት ከተለያዩ አገራት ከ8 ነጥብ ስድስት ሚሊየን በላይ ሰዎች ሲፈናቀሉ፤ በአውሎ ንፍስ የተነሳ ደግሞ ከ 7 ነጥብ አምስት ሚሊየን በላይ አካባቢያቸውን ጥለው ለመሰደድ ተገደዋል።
በዚህ ረገድ፤ ከዓለም ዘጠነኛ ከአፍሪካ ደግሞ ሁለተኛ ደረጃ የያዘችው ኢትዮጵያ ወደ 434,000 ሕዝቦቿ በጎርፍና በሌሎች የተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት ተፈናቅለዋል። ይህ በአገሪቷ ያሉትን በብሔር ተኮር ጥቃት ምክንያት የተፈናቀሉትን ሰዎች ጨምሮ በአገሪቷ ያሉትን ተፈናቃዮች ቁጥር ወደ 2 ነጥብ ስምንት ሚሊየን ከፍ ያደርገዋል። ባለፈው ዓመት ብቻ ከ 1 ነጥብ አራት ሚሊየን በላይ ሰዎች በብሔር ተኮር ጥቃት ምክንያት መፈናቀላቸው ይታወሳል።

ቅጽ 1 ቁጥር 7 ታኅሣሥ 20 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here