ኤርትራ ወደ ሶማሊያ ወታደር ልትልክ ነው መባሏን አስተባበለች

0
975

ኤርትራ በመጪው የካቲት ወር አምስት ሺሕ የሚሆኑ ወታደሮቿን ወደ ሶማሊያ ልትልክ ነው መባሉን አስተባበለች።
እንደ ኢንዲያን ኦሽን ጋዜጣ ዘገባ አገሪቱ ወታደሮቿን የምትልከው በሶማሊያ ለሚገኘው የአፍሪካ የሠላም አስከባሪ (አሚሶም) እርዳታ ነው።
ዘገባው ስሕተት መሆኑን በይፋዊ የማኅበራዊ ገጹ የገለጸው የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ‹‹ውሸት ነው›› ሲል አስተባብሎታል። በዘገባው ላይ ባስቸካይ እርማት እንዲወሰድም ሚንስቴሩ ጋዜጣውን ጠይቋል።
በሶማሊያ ኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዩ የአፍሪካ አገራት ወታደሮቻቸውን ወደ አገሪቱ በመላክ የሠላም ማስከበር ሥራዎችን እየሠሩና ጽንፈኛው የሽብር ቡድን አልሸባብ እያዳከሙት እንደሆነ ይነገራል። በዚህኛው የሠላም ማስከበር ተልዕኮም ብዙ ወታደሮችን ካዋጡ አገራት ኢትዮጵያ አንዷ ናት።
ባለፈው ዓመት የአፍሪካ ኅብረት በሶማሊያ የሚገኘው አልሸባብ እየተዳከመ መምጣቱንና ሱማሊያ በራሷ አቅም ጸጥታዋን ማስከበር የምትችልበት አቋም ላይ እንድትደርስ ለማብቃት በሚል አገራት በስፍራው ያሰማሯቸውን የወታደሮች ቁጥር እንዲቀንሱ የሚል እቅድ ማውጣቱም ይታወሳል።

ቅጽ 1 ቁጥር 7 ታኅሣሥ 20 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here