አምስት ሴቶችን ያካተተው የአምባሳደሮች ሹመት ይፋ ሆነ

0
693

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ኢትዮጵያን በተለያዩ የውጭ አገራት የሚወክሉ 19 አምባሳደሮችን ሹመት ማጽደቃቸው ይታወሳል። አዲስ ከተሾሙት አምባሳደሮች መካከል አምስቱ ሴቶች መሆናቸውም ተገልጿል።
በዚህም መሠረት ሙሉ ሰለሞን በጀርመን በርሊን፣ ሳሚያ ዘካሪያ በኳታር ዶሃ፣ ትዝታ ሙሉጌታ በሕንድ ኒውደልሂ፣ ዓለምፀሃይ መሠረት በኡጋንዳ ካምፓላ እንዲሁም ናሲሴ ጫሊ በካናዳ ኦታዋ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ተሾመዋል።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት ፍጹም አረጋ በአሜሪካ በዋሽንግተን ዲሲ ባለ ሙሉ ሥልጣን አምባሳደር በመሆን ካሳ ተክለብርሃንን ተክተዋል። የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ የነበሩት መለስ ዓለም በኬኒያ ናይሮቢ መሾማቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 7 ታኅሣሥ 20 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here